Disposal, scrap and surplus sales

ተስፋ ለሕፃናት ድርጅት ያገለገሉ ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችንና ለመለዋወጫ የሚያገለግል አንድ ሞተር ሳይክል ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች

የጨረታ ማስታወቂያ

ተስፋ ለሕፃናት ድርጅት በኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አዋጅ ቁጥር 1113/2019 ዳግም ተመዝግቦ በልዩ ልዩ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ የማህበረሰብ ከፍሎችን የድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎት በመስጠት፣ እንዲሁም በማህበረሰብ ልማት ላይ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመተግበር ላይ የሚገኝ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፤በሐረር ከተማ በሚገኘው የምስራቅ ማስተባበሪያ ቢሮአችን ውስጥ የሚገኙ ያገለገሉ ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችንና፣ ለመለዋወጫ የሚያገለግል አንድ ሞተር ሳይክል ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች።

  1. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) እየከፈሉ ሐረር ከተማ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው መዶብ ቢዝነስ ሴንተር 2ኛ ፎቅ በቅርንጫፍ ቢሮአችን በመምጣት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡ አሽናፊ ለሆኑት የጨረታ ማስከበሪያው በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ የሚታሰብ ይሆናል፡፡ ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ ሲፒኦ ወዲያው ተመላሽ ይደረጋል።
  3. ተጫራቾች አሽናፊ መሆናቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉበትን ዋጋ በ5 ቀናት ከፍለው በ5 ቀን ውስጥ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣ ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
  4. ተጫራቾች ስለ ንብረት አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 5፡30 ላይ ተጫራቾች/ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  6. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111222621/0916891300 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
  7. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተስፋ ለሕጻናት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-13
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-08-13 11:30
  • Region: Hareri
  • Publishing entity: Hope for Children Organization
  • Buyer address: Gullele Subcity worda 11 House No. 162 around Mene to Shiromeda road above « Tsehay Chora Elementary School »
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 31, 2026)
  • Posted at: 2026-07-31T08:35:12.000Z
← Back to all tenders