Office furniture

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው መስተዳድር ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች እና የሆቴል አገልግሎት ለማግኘት ለ2019 በጀት አመት በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው መስተዳድር ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች እና የሆቴል አገልግሎት ለማግኘት ለ2019 በጀት አመት በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና፤ የዘመኑን ግብር ከፍሎ አለበት ማጠናቀቁንና፤ ጨረታ ላይ እንዲሳተፍ የሚል ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር መረቀት ማቅረብ

3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጽ/ቤቱ ስም ሲንቄ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1054551161211 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት በጽ/ቤቱ የግዢ የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

5. አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው።

6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ፎቶ ከፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) ሲሆን በጥቃቅን ና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በተደራጁ የትኛውንም የዋስትና ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።

8. ተጫራቾች ሰነዳቸውን ቴክኒካ እና ፋይናንሻል ለየብቻ ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት። ቴክኒካሉን ያለፉት ተወዳዳሪዎች ፋይናንሻላቸው ይከፈታል።

9. የእስቴሽነሪ እና የፅዳት እቃዎችን ለማቅረብ የምትወዳደሩ ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።

10. ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በአዳማ ከተማ ገንዘብ/ፅ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ገዢ ክፍል ውስጥ ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።

11. የጨረታው አሸናፊ ዕቃዎቹን እስከ አዳማ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዘው ማቅረብ አለባቸው።

12. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያ ና በስልክ እንደተገለፀ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ከአዳማ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት ጋር መፈራረም አለበት። ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ገቢ ይሆናል።

13. ማንኛውም ተጫራች ለውድድር የሚቀርበው ቫት ተጠቃሚ ሲሆን ፣ 7.5 % በክፍያ ጊዜ የሚቀነስ ይሆናል።

14. መስሪያ ቤቱ ከሚያደርገው የግዢ ዉል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ መገንዘብ አለበት።

15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-73-33-45-15 በስራ ሰዓት ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-19
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-19 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Adama City Finance and Economic Cooperative Bureau
  • Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
  • Posted at: 2026-08-01T07:29:59.000Z
← Back to all tenders