Stationery and office consumables

የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ማስታወቂያ

የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በሀላባ ዞን ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት ፡-

  1. ሎት 1 አላቂ እና ሌሎች አላቂ እቃዎች
  2. ሎት 2 የደንብ ልብስ
  3. ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ
  4. ሎት4 ፈርኒቸር
  5. ሎት 5 የተለያዩ CC ያላቸው ሞተሮች እና ኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክሎችንይጨምራል 
  6. ሎት 6 የህትመት ሥራ (ባነር፣ ባጅ፣ መታወቂያ፣ የቢሮ ማሕተሞች፣ የኃላፊ የስም ቲተር፣ ሰርተፊኬት)
  7. ሎት7 የሀላባ የባህል አልባሳት የወንድና የሴት
  8. ሎት 8 እስታንዳርዱ የተጠበቀ የቢሮ መጋረጃ
  9. ሎት 9 የሀገር ውስጥ እና የውጪ ምንጣፍ
  10. ሎት 10 የተለያዩ ጌጅ ቆርቆሮ
  11. የተለያዩ የፈረስ ጉልበት ያላቸው ጀነሬተሮች
  12. የተለያዩ የመኪና እስፔሮች (ዝርዝሩን የሽያጩ ሰነድ ላይ ያገኙታል)
  13. የተለያዩ የመኪና አካል ጥገና የሰርቪስ ዋጋ (ዝርዝሩን የሽያጩ ሰነድ ላይ ያገኙታል)
  14. የጡብ ማምረቻ ማሽን (ፒስተን ፓምፕ ሀይድሮ ሊክ ቫልቭ)

ስለዚህ

1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ (ታክስ ክሊራንስ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ተጨማሪ መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሠረት ይሆናል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ21 ተከታታይ የሥራ ቀን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን እያንዳንዱን በብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ።

3. ጨረታው በ22ተኛው ቀን የጨረታው ሳጥን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። ሆኖም ግን በመክፈቻው ቀን የተጫራቾች አለመገኘት መምሪያው ጨረታውን ከመክፈት የሚያስተጓጉለው ነገር አይኖርም።

4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ ዋስትና በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።

5. የጨረታው አሸናፊ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ 10% የውል ማስከበሪያ (CPO) ወይንም አንኮንዲሽናል ባንክ ጋራንት ማስያዝ ይኖርበታል።

6. ጨረታው መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።

7. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ሀላባ ቁሊቶ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ22ተኛው ቀን የጨረታው ሳጥን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-26 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ22ተኛው ቀን የጨረታው ሳጥን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Halaba Zone Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ሎት ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር)
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ 400 (አራት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
  • Posted at: 2026-08-01T07:36:46.000Z
← Back to all tenders