Stationery and office consumables

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የሎዴ ሄጦሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል አላቂ የጽ/መሣሪያዎች፣ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽ/እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እንዲሁም የመኪና እና የሞተር ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2019

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የሎዴ ሄጦሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል አላቂ የጽ/መሣሪያዎች፣ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽ/እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና እና የሞተር ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም

1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ከፍለው፣ የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱና በፌዴራል ወይም በክልል ገንዘብ ጽ/ቤት በአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡበትን የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ዋናውን እና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡

2. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ሁሩታ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡

3. ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000 (አስር ሺህ ብር ብቻ), በአቅራቢያችሁ የሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ ወይም ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ 

4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 / አራት መቶ/ ብር ብቻ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ የጽ/ቤቱ የግዥና ንብረት የሥራ ጉዳይ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

5. በዋጋ አጻጻፍ ተራ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ የተደለዘው ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡ በተጨማሪም በእርሳስና ቀለም በሚጠጣ ብዕር እንዲሁም ከተሰጠው ቦታ ውጪ የተፃፈ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡

6. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7.ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 15 የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታውም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15 የሥራ ቀን 6 ሰአት ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 8 ሰአት ጽ/ቤቱ ለአመቺነቱ በመረጠው ቦታ ይከፈታል፡፡ 

8. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው የእቃ ዋጋዎች የመወዳደሪያ ሃሳቦች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ መካተቱንና አለማካተቱን መግለዕ ይኖርባቸዋል። ይህ ያልተገለጸ ከሆነ፡ የተሰጠው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዳከተተ ይወሰዳል::

9. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0913 395 634, 0934 951 727,09 20 389 358
በአርሲ ዞን የሎዴ ሄጦሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-18
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 15 የሥራ ቀናት 6 ሰአት
  • Bid opening: 2026-08-18 14:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 15 የሥራ ቀናት 8 ሰአት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Arisi Zone Lode Hitosa Woreda F/E/D/B
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ሰነድ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ 400 (አራት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
  • Posted at: 2026-08-01T07:45:58.000Z
← Back to all tenders