Office furniture
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋ/ጽ/ቤት ለጽህፈት ቤቶች መገልገያ አላቂ የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና የተለያዩ የደንብ ልብስ እና ስፌት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2019
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ıኛ ዙር ለጽህፈት ቤቶች መገልገያ አላቂ የቢሮ መገልገያ እቃዎች የጽዳት እቃዎች እና የተለያዩ የደንብ ልብስ እና ስፌት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
- ሎት 01/ የአላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት 02/ የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 03/ የደንብ ልብስ ዕቃዎች
- ሎት 04/ / የደንብ ልብስ ስፌት በግልጽ ጨረታ አወደድሮ መግዛት ይፈልጋል በመሆኑም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል-
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ የአቅራቢነት ሊስት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የሚወዳደሩት በሚያመርቱ እቃ ወይም ተጨማሪ እሴት ለጨመሩት እቃ ሲሆን ከዚህ ውጭ ለሆኑ እቃዎች የሚወዳደሩት እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛትና ሲፒኦ(cpo)በማስያዝ ይሆናል፡፡ ተወዳዳሪዎች በሚያመርቱት እቃ ሲወዳደሩ እና ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ሲያመጡ ልዩ ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
- የመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን በጉለሌ ክ/ከተማ ከወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት ሰነዱን በማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300 ( ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀናት አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆያል።
- ጨረታው በአስረኛው ቀን 10፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን 3:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጡት ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይኸውም
- ሎት 01/ የአላቂ የቢሮ ዕቃዎች የሚሆን ብር 15,000 ( አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ሎት 02/ የጽዳት ዕቃዎች የሚሆን ብር 20,000 (ሀያ ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ሎት 03/ የደንብ ልብስ ዕቃዎችና የሚሆን ብር 10,000(አ ስ ር ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ሎት 04/የደንብ ልብስ ስፊት የሚሆን ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና የማቅረብ ግደታ ይኖርባቸዋል የሚቀርቡትም ናሙናዎች ተፈተው የሚታዩ መሆናቸውን ተጫራቾች ማወቅ አለባቸው።
- ተጫራቾች በአማራጭ ገበያ መጠቀም የተከለከለ ነው።
- ተጫራቾች የአሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወረዳ ግቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት የአሸነፉበትን ዋጋ መጠን እና ብዛት 25 % ተጨማሪ ትዕዛዝ መጠየቅ የሚችል መሆኑ መታወቅ አለበት።
- መ/ቤቱ ከውል በፊት እንደ አስፈላጊነቱ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ እንደሚችል መታወቅ አለበት።
- የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው ሁለቱም ፖስታዎች አንድ አይነት ሰነድ ሞልተው መያያዝ አለበት
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
አድራሻ፡-ስድስት ኪሎ ከፍ ብሎ ስብሰባ ማዕከል አጠገብ ወደ ሐምሌ19 መናፈሻ ሳይደርስ 50 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- 011-1-23-43-69 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፋ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-12
- Bid closing time: 16:30
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀናት አንስቶ በአስረኛው ቀን 10፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-13 09:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀናት አንስቶ በአስራ አንደኛው ቀን 3:30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፋ/ጽ / ቤት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
- Posted at: 2026-08-01T07:54:36.000Z