Property and building foreclosure

ስፋቱ 58.7 ካ/ሜ የሆነ 40/60 ኮንደሚኒየም ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/መ/ቁ/03-36636 የፍ/ስፈ/መ/ቁ/45339

የፍ/ባለመብት ዶ/ር ዘላለም ተመስገን እና የፍ/ባለዕዳ አምሳለ ደምሴ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/03-36636 በ18/04/2016ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/173880 በ27/04/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ ከተማ ወረዳ 12 ቦሌ ቡልቡላ ሳይት 2 ብሎክ 38 የቤት ቁጥር BBL2-B38/HN/408 የሆነ የይዞታ መለያ ቁጥር AA00006120740403804008 ተመዝግቦ የሚገኝ 40/60 ኮንደሚኒየም ቤት ስፋቱ 58.7 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,310,549 ( ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ አስር ሺህ አምስት መቶ አርባ ዘጠኝ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 28 ቀን 2018ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻስን።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid opening: 2026-09-03 11:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
  • Posted at: 2026-08-01T07:57:56.000Z
← Back to all tenders