Property and building foreclosure

የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ደለሉ ገብሬ እና የፍ ባለዕዳ እነ ወ/ሮ ጥሩ ወርቅ ታደሰ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 139403 በ22/08/2016 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ 143172 በ26/09/2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤት ቁጥር 360 በሆነው መኖሪያ ቤት ግቢ ውስጥ በተጠሪ መሰራታቸው ተረጋግጦ የተጠሪ የግል ሀብት ናቸው ከተባሉት ሶስት ክፍል ቤቶች ውጪ ያለው ቤትና ይዞታ የካርታ ቁጥር ኮ/ቀ/የማ/ኃ/መ/60/16338/00 የሴሪያል ቁጥር 074387 በወ/ሮ ደለሉ ገብሬ ስም የተመዘገበ የቦታ ስፋት 251 ካ/ሜ ፍርድ ያረፈበት ቤት ስፋት 153.78 ካ.ሜ የሆነ ቤቱ ቦታው በአካባቢው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ጥናት መሰረት 12.54 ካ/ሜ ይነካዋል። አዋሳኞች በስተሰሜን መንገድ በስተደቡብ የግል ቤት በስተምስራቅ የግል ቤት በስተምዕራብ የግል ቤት የሚያዋስኑት ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 8,384,643.50 (ስምንት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማንያ አራት ሺህ ስድስት መቶ አርባ ሶስት ከ50/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንበረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፈፍ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ አፈ ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid opening: 2026-09-02 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
  • Posted at: 2026-08-01T07:59:17.000Z
← Back to all tenders