Stationery and office consumables
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ልዩ ልዩ ወረቀቶችን፣ Green light balacren, A3 & A4 Kaki posta በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የሀገር ውስጥ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር፡- ልዩ ልዩ ወረቀቶችን፣ Green light balacren, A3 & A4 Kaki posta በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስከር ወረቀት፣ የንግድ ሰርተፍኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ቢሮ ቁጥር 101 በመከፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሯችን መግዛት ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2% በባንከ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከግዥ ከፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ።
5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ/የግዢ ክፍል ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን በዝግ ቀን ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
6. ሁሉም ተጫራቾች ለጥራት ሙከራ የሚሆን ናሙና ጨረታው በሚከፈትበት እለት ወይም አስቀድመው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ዝርዝር አፈጻጸሙም ለካኪ ፖስታ የሚሳተፉ ተጫራቾች በቀረበው ናሙና መሰረት ክብ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
7. ለወረቀቶች የሚሳተፉ ተጫራቾች ለጥራት ሙከራ የሚሆን በቂ ናሙናዎችን በእያንዳንዱ ናሙና ጫፍ ላይ ክብ ማህተም በመምታት በA3 ፖስታ አሽገው ማምጣት አለባቸው።
8. ለባራክረን የሚሳተፉ ደረጃውን የጠበቀ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
9. ሁሉም ተጫራቾች ለሚሳተፉበት ግብአት እቃው ከመጋዘን ያላቸው ወይም ውል በተፈረመ ቢዘገይ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
10. ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር.........0111 515 50 05 / 0115 518 872
ፋክስ....0115 518 696
ፖ.ሳ.ቁጥር... 2365
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-08-15
- Bid closing time: 09:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-15 09:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15ኛው ቀን ከረፋዱ በ3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bole Printing P.L.C.
- Buyer address: ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
- Posted at: 2026-08-01T09:03:53.000Z