Stationery and office consumables
በኢሉአባቦር ዞን የዳሪሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2019 ዓ ም የበጀት ዘመን በሥሩ ላሉት መሥሪያ ቤቶች ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢሉአባቦር ዞን የዳሪሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2019 ዓ ም የበጀት ዘመን በሥሩ ላሉት መሥሪያ ቤቶች ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
- የጽህፈት መሳሪያዎች
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- የፅዳት ዕቃዎች
- የቢሮ ዕቃዎች ወይም ፈርኒቸሮችን
- የደንብ ልብሶች
- የተለያዩ ጎማዎች
- የተለያዩ ህትመቶች
- የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን
በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችዋል
1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበረያ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ቼክ ወይም ሲፒኦ ከውድድር ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
5. የደንብ ልብስን በተመለከተ ግዢው ጥራትን መሠረት በማድረግ ስለሚገዛ የምትወዳደሩ ነጋዴዎች የሚታቀርቡትን ዕቃ ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨርታ ውጪ ይሆናል።
6. የቫት እና TIN NO ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
7. በህጋዊ መንገድ ስለመደራጀታቸው በአቃቤ ህግ የተመሰከረ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
8. አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ሥራ አፈፃፀም የጠቅላላ ዋጋውን 20% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች ሰነዱን ሲያስገቡ ስም፣አድራሻ፣ ፈርማ ያለበት እና አርጅናል እና ኮፒ ሰነድ ማምጣት አለበት።
10. ተጫራቾች ከአሸነፉ በኋላ ውል ለመፈራረም ፈቃደኛ የሆነ እና እቃውን ሲያስገቡ ጥራቱን የጠበቀ መሆን አለበት።
11. ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን አንስተው ለተከታታይ ለ 25 ሃያ አምስት የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ከኢሉባቦር ዞን ዳሪሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመውሰድ ሁሉንም ሰነድ በሶስት መቶ ብር መግዛት ይችላሉ።
12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በ 27/12/2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል.
13. የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 27/12/2018 ዓ.ም በ 8፡30 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል።
14. የዕቃው ማስረከቢያ ቦታ ዳሪሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሆኖ ጠቅላላ ወጪ የሻጩ ግዴታ ይሆናል።
15, በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
16. ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
17. የዕቃው ብዛት ከውድድር በኋላ የሚገለፅ ይሆናል።
18. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
19. ከተራ ቁጥር 1-18 በተጠቀሰው ያልተስማማ በጨረታው መሳተፍ የለበትም።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 91 197 0658/ 09 17 27 68 80 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
በኢሉአባቦር ዞን የዳሪሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-09-02 14:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Illuababora Zone Darimu Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T08:09:19.000Z