Stationery and office consumables
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለቢሮ መገልገያና ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2019
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለቢሮ መገልገያና ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ምድብ 1 አላቂ የጽህፈት ዕቃዎች
- ምድብ 2 የጽዳት ዕቃዎች
- ምድብ 3 ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ ዕቃዎች
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ።
1. በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (TIN N0) ያላቸው።
2. የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና የጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከሀገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት የሚሰጣቸውን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
3. በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ግብር ከፋይነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች ለምድብ 1 ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ)፣ ለምድብ 2 ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ)፣ እና ለምድብ 3፡ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ) የጨረታ ማስከበሪ (Bid Bond) ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 26/12/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በዚሁ ቀን 26/12/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል።
7. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ምድብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከድርጅቱ ግዥና ትራንስፖርት ክፍል ቢሮ ቁጥር 11 መውሰድ ይችላሉ።
8. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ምድብ ናሙና የማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- 011 552 5405/ 011 551 3288
ፖ.ሣ.ቁ 3375 አአ
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-09-01
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-01 10:05
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Petroleum Supply Enterprise
- Buyer address: ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ ስልክ ቁጥር 011-551-3288 ፖ.ሣ.ቁ 3375 አአ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T08:22:36.000Z