Stationery and office consumables

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ስር የሚገኘው የልቤ ፋና ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ስር የሚገኘው የልቤ ፋና ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2019 የበጀት አመት ከዚህ በታች ያሉትን እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 - የደንብ ልብስ
  • ሎት 2- የጽህፈት መሳሪያዎች እና የፅዳት አቃዎች
  • ሎት 3 - አላቂ የት/ት እቃዎች
  • ሎት 4- የኮምፒውተር እና የፎቶ ኮፒ እና የማስተር ጀስትነር ጥገና
  • ሎት 5፡- የሰራተኛ ክበብ

1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ

4. በአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው

5. ናሙና ለሚጠይቁ እቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

6. አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር በባንክ የተረጋገጠ 10000.00 ብር ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ በመሙላት ዘወትር የሥራ ቀናት በስራ ሰአት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

9. የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናሉ እና ኮፒው ተለይቶ በሁለት በተለያዩ ፓስታ ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው።

10. የሚከፈተው ኮፒው ስለሆነ ማንኛውም ማስረጃ ሲፒኦ የመሳሰሉት ሰነዶች ጨረታ ሰነዱ ኮፒ ውስጥ ተጨምሮ መመለስ አለበት።

11. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን እቃዎች ናሙናዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ካላቀረቡ ከጨረታው የምትሰረዙ መሆኑን እናሳውቃለን።

12. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

13. ጨረታው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ሰአት የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል። የበአልም ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይዘዋወራል።

14. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ካዛንቺስ ንግድ ባንክ ወረድ ብሎ ልቤ ፋና ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ተጫራቾች ለተጫረቱባቸው እቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 551-8669 መደወል ይቻላል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት በቂርቆስ
ክፍለ ከተማ የልቤ ፋና ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-11
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ11፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-08-12 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Libe Fana School
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
  • Posted at: 2026-08-03T08:38:42.000Z
← Back to all tenders