Property and building foreclosure

የቦታ ስፋት 72 ካ.ሜ የሆነ ጂ+2 እና የቦታ ስፋት 43 ካ.ሜ የሆነ ጂ+2 የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት ወ/ሮ ፋንታዬ ዘለቀ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ጌታሁን መኮንን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/119804 በ30/8/2015 ዓ/ም እና በኮ/ መ/ቁ/164759 በ02/03/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ውስጥ የሚገኝ የካርታ ቁጥር ቦሌ2/37/10/13/12238/00 የሰሪያል 002036 የሆነ ጂ+2 በአቶ ጌታሁን መኮንን ሲሳይ ስም የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታ ስፋት 72 ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 7,221,120 (ሰባት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃያ አንድ ሺህ አንድ መቶ ሃያ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። 2ኛ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ውስጥ በአመልካች ስም በካርታ ቁጥር በቦሌ10/57/1/2/54403/00 የሰሪያል 101877 የሆነ ጂ+2 በፋንታዬ ዘለቀ ታችበሌ ስም የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታ ስፋት 43 ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 4,476,128 ( አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሰባ ስድስት ሺህ አንድ መቶ ሃያ ስምንት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀንጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ

የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

 


Tender details

  • Deadline: 2026-09-04
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-09-04 14:00
  • Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
  • Posted at: 2026-08-03T10:43:41.000Z
← Back to all tenders