Stationery and office consumables
የሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አላቂና ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎችን፣ የጽዳት እቃዎችን፣ የሰራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- አላቂና ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፤
- ፈርኒቸር፤
- የጽህፈት መሣሪያዎችን፤
- የጽዳት እቃዎችን ፤
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ እና
- የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም:-
- ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ከፍለው፣ የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱና በፌደራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዥዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ እና የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው እንዲሁም፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች፤ ለጽህፈት መሣሪያዎች፤ ለፅዳት እቃዎች፤ለደንብ ልብስ፤ ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በጽ/ቤቱ ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000175073578 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጽ/ቤ ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ የጽ/ቤቱ የግዢ፤ የንብረትና ፋይናንስ የሥራ ጉዳይ ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመከፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታውም በ16ኛው የሥራ ቀናት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ
- ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጽ/ቤቱ ለአመቺነቱ በመረጠው ቦታ ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለቋሚ የቢሮፈርኒቸር እቃዎች እና ለጽህፈት መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ብር 35000.00 (ሰላሳ አምስት ሺህ) እንዲሁም፤ ለጽዳት እቃዎች ፤ለደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ብር 25000.00 (ሃያ አምስት ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. (C.P.O.) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል።
- አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ በወረዳው ውስጥ በሚገኘው ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር (09 62 67 14 08)( 09 08 39 40 66) ይጠይቁ።
በአርሲ ዞን የሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-19
- Bid closing time: 10:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀናት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-19 11:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀናት ከቀኑ 5፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Honkolo wabe Wereda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T10:54:08.000Z