Stationery and office consumables

የጅማ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎችን፣ የጽህፈት መሣሪያዎችን፣ የጽዳት እቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና ጎማ እና ባትሪ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጅማ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በዞን ደረጃ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉትን

  • የተለያዩ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎችን፣
  • የጽህፈት መሣሪያዎችን፤
  • የጽዳት እቃዎችን ፣
  • የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና
  • ጎማ እና ባትሪ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የቀረቡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሣተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን ። በዚህ መሠረት

ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚገባቸው መመዘኛዎች :-

  1. ለሥራ ዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ
  2. ግብር ከፋይ ምዝገባ ማለትም Tin No ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችልሉ፣
  3. በአቅራቢነት ለመሣተፍ የተመዘገበ ከፌዴራል ገንዘብ ሚ/ር ወይም ከክልል የገንዘብ ቢሮ የተሰጠ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
  4. ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴትታክስ /VAT/ለመሰብሰብ የተመዘገቡና የMAI ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. የዘመኑን ግብር የከፈሉና Tax ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣
  6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሠነድ ለእያንዳንዱ ጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 ( አምስት መቶ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ጽ/ቤቱ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 መውሰድ ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለጽህፈት መሣሪያዎች የኢትዮጵያ ብር 10,000.00 ( አስር ሺህ ) ብር፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና ጎማ እና ባትሪ እቃዎች የኢትዮጵያ ብር 15000.00 (አስራ አምስት ሺህ) እና ለጽዳት እቃዎች ደግሞ ብር 7000.00(ሰባት ሺህ) በጅማ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በባንክ በተመሠከረለት ሲፕኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የሚያቅርቡት መወዳደሪያ ዋጋ ታክስን (VAT) አጠቃሎ የተሠራና በአፋን ኦሮሞ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ተዘጋጅቶ በቀረበው ፎርማት መሠረት በታይፕ ወይም በቀለም ሞልተው መመለስ አለባቸው :: የጨረታውን ሠነድ ሞልተው በታሸገ ፖስታ አድርገው በተዘጋጀው የጨሪታ ሣጥን ማስገባት አለባቸው።
  9. የቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናል ሲፒኦ (CPO) ጋር ታሽጎ ቴክኒካል ኮፒ ዶክመንት ጋር የጨረታ ዓይነት ተገልጾ በሁለቱ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ስምና አድራሻ ተፅፎ በአንድ ፖስታ ይገባል ።
  10. የፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናል በፖስታ ታሽጎ ከፋይናንሻል ኮፒ ዶክመንት ጋር የጨረታ ዓይነት ተገልጾ በሁለቱ ፖስታ ለይ የድርጅቱ ስምና አድራሻ ተፅፎ በአንድ ፖስታ ይገባል ።
  11. የጨረታ ሣጥን መዝጊያና መክፈቻ ሰዓቱን እና ቀን አስመልክቶ ሠነዶቹን መሸጫ ቀን ካበቃበት ዕለት በኋላ በሚቀጥለው የመጀመሪያ የሥራ ቀን ከጠዋቱ ልክ በ4፡00 ሠዓት የጨረታ ሣጥን ተዘግቶ በዚያንኑ ቀን ልክ በ4፡30 ይከፈታል
  12. ጽህፈት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
  13. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለመግዛት ሲመጡ ከላይ 1-5 ተራ ቁጥር የተጠቀሰውን ቴክኒካል መረጃ እና
  14. ኮፒ መያዝ አለባቸው።
  15.  ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 047 111 1193 ወይም 047 111 0380 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የጅማ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-11
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በሚቀጥለው የመጀመሪያ የሥራ ቀን ከጠዋቱ ልክ በ4፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-08-11 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በሚቀጥለው የመጀመሪያ የሥራ ቀን ከጠዋቱ ልክ በ4፡30 ሠዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: JImma Zone FEDB
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
  • Posted at: 2026-08-03T11:02:40.000Z
← Back to all tenders