School uniforms
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የብሔራዊ ቅድመ አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ የደንብ ልብስ፣ የስፖርት መምህራን ትጥቅ፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች እና የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ የልብስ ስፌት፣ ልዩ ልዩ ጥገና እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የብሔራዊ ቅድመ አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ የደንብ ልብስ፣ የስፖርት መምህራን ትጥቅ፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች እና የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ የልብስ ስፌት፣ ልዩ ልዩ ጥገና እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
1. በመንግሥት የአቅራቢ ስም ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. የጨረታ ሰነዱን 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከፍሎ በመግዛትና ሰነዱ ላይ ዋጋውን በመሙላት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በብሔራዊ ቅድመ አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛ (አስረኛ) ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
5. ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ ለደንብ ልብስ 2,500.00 (ሁለት ሽህ አምስት መቶ ብር) ለአላቂ የትምህርት እቃዎች 4,500(አራት ሽህ አምስት መቶ ብር) ለፅዳት እቃዎች እና ህትመት 2,000.00 ( ሁለት ሽህ ብር) ለቋሚ እቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ 5000(አምስት ሽህ ብር) በብሔራዊ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት ስም ሲፒኦ (cpo) በማሠራት ኮፒው ውስጥ በማስገባት ማረጋገጫቸውን ከማወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ቢሮ ቁጥር 02 ይከፈታል፤ ቀኑ በዓል ወይም ከሥራ ቀን ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
7. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ አለባቸው።
8. ተጫራቾች አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት የለባቸውም።
9. ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
10. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ኮፒ በማድረግ እና የተጠየቁትን ማስረጃዎች ኮፒ እና ዋናውን ለየብቻ በማሸግ ሁለቱንም በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
11. የሚሞላው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት።
12. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በስተጀርባ ብሔራዊ ቅድመ አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት።
ስልክ ቁጥር ፡- 011 557-3784
በቂርቆስ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የብሔራዊ ቅድመ አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-11
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-11 12:00
- Bid opening (note): የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በቂርቆስ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የብሔራዊ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
- Buyer address: አዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በስተጀርባ ብሔራዊ ቅድመ አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T13:29:31.000Z