School uniforms

አፍሪካ አንድነት ቁ.1 አጸደ ህጻናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት ደንብ ልብስ፣ አላቂ የት/ት እቃ፤ የህክምና እቃ፣ የጽዳት እቃ፤ ዝቅተኛ ቋሚ እቃ፤ ፕላንትና ማሽነሪ፤ ህንጻና ቁሳቁስ እና የተለያዩ የጥገና ስራዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01

በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ስር የሚገኘው የአፍሪካ አንድነት ቁ. አጸደ ህጻናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት ልዩ ቦታው አትክልት ተራ ሲሆን በ2019 ዓ.ም

  • የደንብ ልብስ፣
  • አላቂ የት/ት እቃ፤
  • የህክምና እቃ፣
  • የጽዳት እቃ፤ 
  • ዝቅተኛ ቋሚ እቃ፤
  • ፕላንትና ማሽነሪ፤
  • ህንጻና ቁሳቁስ እና የተለያዩ የጥገና ስራዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

 በዚህም መሰረት በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባችኋል።

  • በተሰማሩበት የስራ መስክ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉን፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  • የመንግስት ግዢ ኤጀንሲ የንግድ ምዝገባ ያላቸዉና በአቅራቢነት ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገበ።
  • የመንግስት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ጊዜዉ ያላለፈበት ማስረጃ በ2019 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
  • ከላይ የተጠቀሱትን የእቃዎች ዝርዝር የሚያሳውቅና የግዢ መመሪያ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአፍሪካ አንድነት ቁ1 አጸደ ህጻናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት በስራ ሰአት በመገኝት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዝርዝር ያዘ ሰነድ ከነዋጋዉ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ በት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 01 በሰራ ሰዓት ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል የሚጫረቱበት የእቃ ዋጋዎች 2% በት/ቤቱ ስም የተዘጋጀ ሲፒኦ ወይም በት/ቤቱ ፋይናንስ በጥሬ ገንዘብ በማሲያዝ ማረጋገጫዉን ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች አንዱ ባስገባው ዋጋ ተንተርሶ መስጠት አይችልም።
  • ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰአት ታሽጎ በዛዉ እለት ከቀኑ 4፡30 ላይ በአፍሪካ አንድነት ቁı አጸደ ህጻናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት ቤተ መጽሀፍት ዉስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ይከፈታል።
  • ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ ማህተም በማድረግ በሰም በታሸገ ካኪ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
  • ት/ቤቱ የተሻለ የግዥ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር- 011 057 0295/96 መደወል ይችላሉ።

በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 የአፍሪካ አንድነት

ቁ.1 አጸደ ህጻናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-15
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-08-15 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Africa Andenet No.1 Kindergarten & Elementary School
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 04, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T12:34:33.000Z
← Back to all tenders