Property and building foreclosure
ፀሐይ ባንክ አ.ማ. ለመኖሪያ G+3 ቤት በግልጽ ሐራጅ ጨረታ) አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀሐይ ባንክ አ.ማ. ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ቀጥሎ ባለው ሠንጠረዥ ውስጥ የተመለከተውን ንብረት/ሕንጻ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በአዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታና አሁን በሚገኝበት ይዞታ ላይ እንዳለ በግልጽ ሐራጅ ጨረታ) አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
የንብረቱ አድራሻ |
የቦታ ስፋት |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር |
የንብረቱ ዓይነት /የይዞታ አገልግሎት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
ጨረታው የሚካሄድበት |
ተጫራቾች የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታው ደረጃ |
||||
|
ክልል/ ከተማ |
ክ/ከተማ/ከተ/ማ/ዞን |
ወረዳ/ ቀበሌ |
|||||||||||||
|
ቀን |
ሰዓት |
||||||||||||||
|
1 |
ኔስት አዲስ ዋን ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር |
ወይ. አይዳ በቀለ አበበ |
በቅሎ ቤት |
አዲስ አበባ |
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ከተማ |
01 |
72 |
01/63/27850/00 |
ለመኖሪያ G+3 |
10,978,757.88 |
ነሀሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም |
ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
ከ4፡00 እስከ 5፡30 ሰዓት |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
|
ማሳሰቢያ፦
በሐራጁ(ጨረታ) መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ በፀሐይ ባንክ አ.ማ. (Tsehay Bank S...) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
2. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝጊያ ሰዓት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል። የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ እስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል። የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በባንኩ የሚመለከተው አካል ፀድቆ የጨረታ አሸናፊ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲሰጠው ብቻ ነው።
3. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤ በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለጨረታ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ክፍያ ማዘዣ (CPO) ይመለስላቸዋል።
4. ንብረቱን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘብ ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም። ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቱን ካልተረከበ ከንብረቱ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።
5. የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ማናቸውንም ክፍያዎችን፣ የሊዝ ክፍያ፤ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችን ይከፍላል። በሽያጩ ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% አይታሰብም።
6. ለሐራጅ ጨረታ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች በማናቻም ቀን በስራ ሰዓት ሕግ አገልግሎት መምሪያ ስልክ በመደወል እና ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ።
7. ባንኩ ስመንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው የመንግስት አካል ተገቢውን የድጋፍ ደብዳቤ ይጽፋል።
8. የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 4 ላንቻ አካባቢ ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት መአዛ ደሳለኝ ሕንጻ የፀሐይ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤትîኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው።
9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የሐራጁ መሰረዝ ለባንኩ ጥቅም ሲባል ሐራጁ ተካሂዶ ከፍተኛ የጨረታ ዋጋ አቅራቢ ከታወቀ በኋላም ሊሆን ይችላል።
10. በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዦች ወይም የእነዚህ ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው። በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ አካል ከሆነ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት ዋና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ቲን ሰርተፊኬት፣ እንዲሁም ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ጽ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የጸደቀ የድርጅቱ መመስረቻ ፅሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፤ቃለ ጉባዔ ወይም ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት። ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል።
11. ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዦች ወይም ህጋዊ ተወካዮች የጨረታውን ሒደት ለመከታተል ከላይ በተጠቀሰው ቦታና ቀን እንድትገኙ እያሳሰብን ካልተገኛችሁ በሌላችሁበት ጨረታው የሚከናወን መሆኑን እንገልጻለን።
12. በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት እና ሕጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅቶችም ያገለግላል።
ለበለጠ መረጃ ፀሐይ ባንክ አ.ማ. ሕግ አገልግሎት መምሪያ
011 470 4915 ወይም +011 470 5354 መደወል ይቻላሉ።
ፀሐይ ባንክ ለሁሉ
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-02 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tsehay Bank S.C.
- Buyer address: Beklobet, Meaza Desalegn Building (In front of Ethiopia Hotel #2), 5th floor
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T15:45:04.000Z