Office furniture

በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የደ/ሊባኖስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለወረዳው እና ለESRP ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የቤት ቆርቆሮ እና ሚስማር፣ ሲሚንቶ፣ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የደ/ሊባኖስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለወረዳው እና ለESRP ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል

  • የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣
  • አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • የጽዳት እቃዎች፣
  • ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • የመኪና ጎማዎች
  • የቤትቆርቆሮ እና ሚስማር ሲሚንቶ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣ የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ፡፡

ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ደብረ ሊባኖስ ወረዳ CPO/ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000/አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ/ ስምምነት መፈራረም ይኖርበታል፡፡

ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ባሸነፈባቸው የእቃ ዝርዝር መሰረት ከመ/ቤቱ ጋር የውል

ተጫራቾች እቃዎቹን ከነ ትራንስፖርት ወጭያቸው የሚሸጡበትን ዋጋና አይነት በመለየት በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ሞልተው በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30-11፡30 ድረስ በስራ ቀናት ውስጥ ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ተዘግቶ በዚህ ቀን በ5፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይካሄዳል፡፡

ተጫራቾች በሚፈልጉትና ማቅረብ በሚችሉበት እቃዎች ላይ ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡ ሆኖም ለአንድ ዓይነት እቃ ከተጠየቀው ብዛት አሳንሶ ማቅረብ አይቻልም፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉበትን እቃዎች ደ/ሊባኖስ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት እቃ ግምጃ ቤት የማጓጓዣ የማስጫኛና የማውረጃ ወጪ መቻል ይኖርባቸዋል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃ አይነት ወይም ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡

ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0963226105 ዘወትር በስራ ሰዓት በመደወል ወይም ደ/ሊባኖስ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት እቃ ግዥ ክፍል በግንባር ቀርበው መረዳት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- ሰሜን ሸዋ ዞን የደ/ሊባኖስ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ከአ/አ በስተ ሰሚን 89 ኪ.ሜ ላይ ይገኛል

ሸረሮ ከተማ

በሰሜን ሸዋ ዞን የደ/ሊባኖስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-20
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-20 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ5፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Debre Libanos Woreda F/E/D/Office
  • Buyer address: በሰሜን ሸዋ ዞን የደ/ሊባኖስ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ፅ/ቤት ከአ/አ በስተ ሰሜን 89 ኪ.ሜ /ደብረጽጌ/
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 03, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T07:24:22.000Z
← Back to all tenders