Property and building foreclosure
ጠቅላላ ስፋቱ 415 ካ.ሜ የሆነ ቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለመብት እነ ወ/ሮ ፈለቀች ፍስሀ እና በፍርድ ባለእዳ እነ አቶ መሰለ ፋንታዬ መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 197553 በ 18/11/2017ዓ.ም 205923 በቀን 5/3/2018ዓ.ም፣ 6/5/2018 ዓ.ም፣ 28/9/2018ዓ.ም፣ 1/11/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ በየካ/ክ/ከተማ ወረዳ 1 የቤት ቁጥር 347 በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቤት እና ይዞታ በካርታ ቁጥር የካ/212463/11 ሴሪ ቁጥር 0650361 በነባር 373ካ.ሜ በሊዝ የተካተተ 42ካ.ሜ ጠቅላላ ስፋት 415ካ.ሜ አዋሳኞች በምስራቅ መንገድ በምዕራብ አቶ ወንድሙ ይርጋ በሰሜን ወ/ሮ ዘነበች ቀስቅሴ በደቡብ አቶ አሸናፊ በቀለ እና አቶ መዝገቡ ኃይሌ የሚያዋስኑት ሆኖ የቤቱ የሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት ብር 8,368,860 (ስምንት ሚሊየን ሶስት መቶ ስልሳ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 28 ቀን 2018ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/ አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-03
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-09-03 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Aug 03, 2026)
- Posted at: 2026-08-04T07:31:22.000Z