Stationery and office consumables

በዳንግላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ/ፋይ/ን/አስ ለሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና ጀነሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ


በዳንግላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ/ፋይ/ን/አስ ለሴክተር መ/ቤቶች

  • የጽህፈት መሳሪያ፣
  • ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • የጽዳት እቃዎች እና
  • ጀነሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 ስለሆነም መጫረት የምትፈልጉ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የግዥዉ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-3 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ተነባቢ በሆነ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ከፍለዉ ዳንግላ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 13 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  6.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 (አስር አምስት ሽህ ብር) በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደ ምርጫችሁ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሊተር ኦፍ ክሪዲት ወይም በመስሪያ ቤቱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተዉ ባንክ ሂሳብ ቁጥር የሚያስገቡ እና ዲፖዚት ስሊፕ ማቅረብ የሚችሉ ወይም በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ገቢ የሚያደርጉ እና ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር ማቅረብ የሚችሉ።
  7. አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 10 በመቶ ዋስትና በቢድ ቦንድ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ እና በባንክ በመስሪያ ቤቱ የሂሳብ ቁጥር ገቢ ማድረግ የሚችል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማ እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ ቡድን ግዥዎች ቢሮ ለጨረታ ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ።
  9. ተጫራቾች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡00 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  10. በ16ኛዉ ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ።
  11. ጨረታዉ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በ4፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል።
  12. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ ወይም እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  13. ስለጨረታዉ ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 221 1610 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
  14. የጨረታዉን ሙሉ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  15. ጨረታው በአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
  16. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች አሸናፊው በሚቀርበው ናሙና መሰረት ማቅረብ ይጠበቀበታል።
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

 የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-18
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-18 10:15
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Dangila City Administration FEDB
  • Bid bond: 15,000 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Aug 03, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T08:43:58.000Z
← Back to all tenders