Stationery and office consumables

በአርሲ ዞን ጉና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና የሰራተኞች የደንብ ልብሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2019 የበጀት ዓመት

በአርሲ ዞን ጉና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር የጽህፈት መሣሪያዎች፤ የጽዳት እቃዎች፣ የሰራተኞች የደንብ ልብሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም:-

1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) ያላቸው እና በፌዴራል፤ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ / ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች እና ለጽህፈት መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ)እንዲሁም፤ ለጽዳት እቃዎች፤ ለሠራተኞች የደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር ብቻ) በጽ/ቤቱ ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000062732109 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የበጀትና ፋይናንስ አስተዳደር የሥራ ጉዳይ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመከፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት : በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 21ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በ21ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ይከፈታል።

5. ተጫራቾች ለዚህ የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ብር 5000.00 (አምስት ሺህ) በታወቀ ባንክ የክፍያ ማዘዣ(C.PO) ብቻ ማስያዝ አለባቸዉ:: የጥቃቅንና አነስተኛ ማይክሮ ኢንተርፕራይዞች ለዚህ የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ከአደረጃቸው መስሪያቤት የጉና ወርዳ ንግድ ሰራ ፈጠራና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ብቻ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።

6. አሽናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ጉና ወረዳ አባጀማ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳው ገንዘብ ጽ/ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር(0927037969/0910773879/
0925473748) ይጠይቁ።
በአርሲ ዞን ጉና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ21ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-27 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ21ኛው የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Arsi Zone Guna Woreda FEDB
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ 5000.00 (አምስት ሺህ ብር)
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Aug 04, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T08:44:54.000Z
← Back to all tenders