Property and building foreclosure

የድርጅት ቤት ሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአፈ/ከሳሽ ምንታምር አዝመራው፣ ጠበቃ ደምስ ሹመቴ እና በአፈ/ተከሳሽ ሰለሞን አስራት መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ፤ በቡሬ ከተማ ቀበሌ 02 የሚገኘው፣ በምስራቅ እና በምእራብ መንገድ ፣በሰሜን ሀሰን ነጋሽ፣ በደቡብ አያሌው ፈንታ መካከል ተዋስኖ የሚገኘው፤1000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚገኝ፤ የድርጅት ቤትና ንብረቱ በግምት መነሻ ዋጋው 22‚500,000 (ሀያ ሁለት ሚሊዩን አምስት መቶ ሽህ ) ብር ሆኖ በጨረታ ይሸጣል የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከሐምሌ 27/2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ ታትሞ ለ30 ቀናት ቆይቶ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 5፡00 ተጫራቾች የሚመዘገቡበት ሰአት ሲሆን፤ጨረታው የሚካሄድበት ሰአት ደግሞ ከ5፡00 እስክ 6፡00 ከፍተኛ ዋጋ ላቀረቡ ተጫራቾች ይሸጣል። ተጫራቾች የግምቱን ¼ኛ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በመያዝ ቡሬ ከተማ ቀበሌ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል።

የቡሬ ወረዳ ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-09-03 12:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Burie Woreda Court
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Be'kur (Aug 03, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T09:03:14.000Z
← Back to all tenders