Stationery and office consumables
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘኣ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በአብቹና ኘኣ ወረዳ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘኣ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በአብቹና ኘኣ ወረዳ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- ህትመቶች፣
- የጽዳት ዕቃዎች፣
- ቋሚ የቢሮ ውስጥ ዕቃዎች፣
- ፈርኒቸሮች፤
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ኮምፒተሮች፣ ጄኔሬተሮች የመሳሰሉትና የመኪናና ሞተር መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የመኪናና ሞተር ጎማ፣ ባትሪዎች፣
- የግንባታ ፣ የውሃ ዕቃዎችና
- የሠራተኞች የደንብ ልብስና ጫማዎች፣
- የተለያዩ የደንና አትክልት ዘሮችን በግለጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. በገንዘብ ሚ/ር የዕቃ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
8. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀትና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያለው።
4. ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የዕቃውን ዝርዝር (SPECIFICATION) ዘወትር በሥራ ሰዓት በአብቹና ኘኣ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በመምጣት ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ መ/ቤቱ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ ሞልተው በሰም በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 4 መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
6. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የሥራ ቀን ሆኖ በዚሁ ቀን በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ ታሽጎ/በ8፡00 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በቀጠዩ የሥራ ቀን 8፡00 ሰዓት በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል።
7. የጨረታው ማስከበሪያ 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረ CPO ማቅረብ የሚችሉ።
8. አሸናፊው ድርጅት ዕቃዎችን አብቹና ኘኣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድርስ በማምጣት ማስገባት አለበት።
9. የተሞላውን ዋጋ ሠርዘው ወይም ደልዘው መጻፍ ክልክል ነው።
10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው።
11. የተጠየቁት ዕቃዎች በሙሉ ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው።
ለበለጠ መረጃ፦ ስልክ ቁጥር 09 13 29 97 65 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘኣ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-20
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የሥራ ቀን ሆኖ በዚሁ ቀን በ6፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-20 14:00
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የሥራ ቀን ሆኖ በዚሁ ቀን በ8፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Abichu and Negna Woreda Finance and Economic Cooperative Bureau
- Bid bond: 15,000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 04, 2026)
- Posted at: 2026-08-04T09:11:54.000Z