Stationery and office consumables
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ስቴሽነሪ (የፅህፈት መሳሪያዎች) ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/ST/103/2026
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ስቴሽነሪ (የፅህፈት መሳሪያዎች) ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
የፕሮጀክት ስም |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1. |
ስቴሽነሪ (የፅህፈት መሳሪያዎች) |
ዋና መ/ቤት |
DCE/ST/ 103/2026 |
ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም 4፡15 ሰዓት |
ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት |
50,000.00 |
ስለሆነም፡-
1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ...ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00(ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ለ120 (አንድ መቶ ሃያ) Calendar days ፀንቶ የሚቆይ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ስነድ በሚያቀርቡበት ወቅት ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች አብሮ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
8. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ
የቀጥታ ስልክ ቁፕር 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114 42-22-70/71/72
E-mail አድራሻ [email protected]
የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ.0114-40-04-71 / 0114-42-07-4
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-08-19
- Bid closing time: 10:15
- Bid opening: 2026-08-19 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
- Buyer address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 04, 2026)
- Posted at: 2026-08-04T10:48:01.000Z