Stationery and office consumables

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ሐረርጌ የጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚውሉ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ 001/2019

በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት በምስራቅ ሐረርጌ የጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት “በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት የመንግሰት መስሪያ ቤቶች የሚውል

  • የጽህፈት መሳሪያዎችና፤ የጽዳት እቃዎች፤ ቐሚ እቃዎች፤ ፈርኒቸር ና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • የግንባታ እቃዎች
  • የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማ ና እቃዎች (spare parts) ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫረቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ስራ ዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት ያላቸውና የዘመኑን ግብር ያጠናቀቁ ወይም ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ኪሊራንስ፣ እነዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የምትወዳደሩበትን የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ጠቅላላ ብር 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ( CPO) በጥሬ ብር ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት ይችላሉ።

4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፉባቸውን እቃዎች በሚደረገው ስምምነት መሰረት በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ።

6. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኃላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦታ ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።

7. የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ ያለው ከሆነ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።

8. ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በጨረታው ውስጥ የተጠቀሱትን የኮምፒውተር ቀለም፣ የኮምፒውተር ወረቀት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ስክሪብቶ ፣ለናሙና አንዳንድ ፍሬ ማምጣት ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች የገዙት እያንዳንዱ ሰነድ ገፅ ላይ ማህተምና ፍርማ ማድረግ አለባቸው።

10. ተጫራቾች ስለሚያቀርቡት እቃ የጥራት ደረጃ ጥራቱ ከሀገር ውሰጥ ጥራት ደረጃ የተረጋገጠ መሆን አለበት።

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ) ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0936 827 918 / 0991 449 196 ደውለው ወይንም መስሪያ ቤታችን ድረስ በመምጣት በጽሁፍም ሆነ በአካል በመገኘት መረዳት ይቻላል።

ማሳሰቢያ፡- መስሪያ ቤቱ አሸናፊውን ለመለየት በጥቅል ወይም በእያንዳንዱ ዋጋ ላይ ተመስርቶ ሊያወዳድር ይችላል።

የጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኃላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-21 14:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኃላ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Jarso Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 04, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T11:10:48.000Z
← Back to all tenders