Property and building foreclosure
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ንብረቶችን በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር፡ AMFI/01/2019
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለው) እና 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረቡትን ንብረቶች በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ. |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
ለሐራጅ የቀረበው ንብረትና ዝርዝር መግለጫ |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር |
ሐራጁ የሚከናወንበት |
ሐራጁ የወጣው |
||||
|
ለሐራጅ የቀረበው ንብረት |
አድራሻ |
የካርታ ቁጥር |
የቦታ ስፋት |
ቀን |
ሰዓት |
||||||
|
1 |
እነ ኃይለማሪያም አግደው (2) ሰዎች |
አቶ መንግስቱ ተስፋዬ |
ፊታውራሪ ገበየሁ |
የመኖሪያ ቤት |
አማራ ከልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ሲያደብርና ዋዩ ወረዳ፣ ደነባ ከተማ፣ ቀበሌ 01 |
ጨ/01/12/09 |
200 ካ/ሜ የተሰራ ቤት ያለበት |
1,850,000 |
ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም |
4፡00-5፡00 |
ለሶስተኛ ጊዜ |
|
2 |
እነ ወ/ሮ ሰላም ጌታቸው (2) ሰዎች |
ወ/ሮ ሰላም ጌታቸው |
ዶ/ር ከበደ ሚካኤል |
የመኖሪያ ቤት |
አማራ ክልል፣ ደ/ብርሃን ከተማ፣ ጫጫ ከተማ 01 ቀበሌ |
3039/14 |
200 ካ/ሜ |
2,700,000 |
ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም |
4፡00-5፡30 |
ለሁለተኛ ጊዜ |
|
3 |
እነ በፍርዱ አይደፍሩህም(2) ሰዎች |
ወ/ሮ እልፍነሽ የሺ |
ዶ/ር ከበደ ሚካኤል |
የመኖሪያ ቤት |
አማራ ከልል፣ ደ/ብርሃን ከተማ፣ ጫጫ ከ/ከተማ፣ ን/ሀ/መለኮት ቀበሌ |
3578/15 |
200 ካ/ሜ |
2,000,000 |
ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም |
5፡30-6፡00 |
ለሁለተኛ ጊዜ |
|
4 |
አልማዝ ከተማ |
አልማዝ ከተማ |
ፕ/ኣስራት |
የመኖሪያ ቤት |
አማራ ከልል፣ ሰ/ሸዋ ዞን፣ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ፣ ባልጪ ከተማ፣ 01 ቀበሌ |
2/7275/2000/9 |
195 ካሜ |
1,950,000 |
ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም |
6፡00-6፡30 |
ለሁለተኛ ጊዜ |
|
5 |
ፀደቅ ወንዳፈረው |
ላቀው ምኒሉ |
ንጉስ ሳህለ ስላሴ |
የመኖሪያ ቤት |
አማራ ክልል፣ ሰ/ሸዋ ዞን፣ አንኮበር ወረዳ፣ ጎረቤላ ከተማ፣ 01 ቀበሌ |
0273/97 |
200 ካ/ሜ |
497,000 |
ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም |
6፡40-1፡00 |
ለሁለተኛ ጊዜ |
|
6 |
ዲ/ን በላይ ካሳሁን |
ወ/ሮ ሳራ አበበ |
አሰላ |
የመኖሪያ ቤት |
ኦሮሚያ ክልል፣ እርሲ ዞን፣ አሰላ ከተማ፣ 04 ቀበሌ |
22745/76/14 |
200 ካ/ሜ |
1,200,000 |
ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም |
4፡00-5፡00 |
ለሁለተኛ ጊዜ |
|
ተ.ቁ. |
የተበዳሪ ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
ለሐራጅ የቀረበው ተሽከርካሪ ዝርዝር መግለጫ |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር |
ሐራጁ የሚከናወንበት |
ሐራጁ የወጣው |
||||||
|
የመያዣ አይነት |
የተሰራበት ሀገር |
የሰሌዳ ቁጥር |
የሻንሲ/ የሲሪያል ቁጥር |
የምርት ዘመን |
የሞተር ቁጥር |
ቀን |
ሰዓት |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
|||||
|
1 |
ሻምበል ምትኬ ሙላቱ |
ሻምበል ምትኬ ሙላቱ |
ሸዋ/ሮቢት |
ባጃጅ |
ህንድ |
አ.ማ-01-88958 |
MD6M14PA3P4K06316 |
2011 |
AK44KP4405563 |
200,000 |
ነሀሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም |
4፡00-5፡00 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
|
2 |
ፍቅሩ መለሰ |
ፍቅሩ መለሰ |
ደ/ብርሃን |
ባጃጅ |
ህንድ |
አማ-01-29535 |
MD2A25BZ4ZWF94783 |
2017 |
AZZWHF48954 |
120,000 |
ነሀሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም |
4፡00-5፡00 |
ለሁለተኛ ጊዜ |
|
3 |
ዘነበ በትረ |
ዘነበ በትረ |
ደ/ብርሃን |
ባጃጅ |
ህንድ |
አማ-01-43949 |
MD2A25BYXKWF97265 |
2019 |
AZZWKF34576 |
70,000 |
ነሀሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም |
5:00-6:00 |
ለሁለተኛ ጊዜ |
|
4 |
ደረጀ ግርማ |
ደረጀ ግርማ |
ደ/ብርሃን |
ባጃጅ |
ህንድ |
ማ-01-36807 |
MCG39P3PBH1819811 |
2018 |
CAC18H0085 |
50,000 |
ነሀሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም |
6:00-6:30 |
ለሁለተኛ ጊዜ |
|
5 |
መላኩ አስቻለው |
መላኩ አስቻለው |
ደ/ብርሃን |
ባጃጅ |
ህንድ |
አማ-01-85631 |
MD6M14PF2N4L01636 |
2022 |
AF4L4501894 |
200,000 |
ነሀሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም |
6:30- 7:30 |
ለሁለተኛ ጊዜ |
የሐራጅ ደንቦች፡-
1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ኢማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
2. አሸናፊ የሆነው ተጫራችያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል አለበት። ካልተከፈለ የተያዘው ገንዘብ ለማይክሮ ፋይናንሱ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል። በጨረታው ተሸናፊ ለሆኑት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል።
3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው ብቻ ናቸው። ተበዳሪ እና ንብረት አስያጁ ወይምወኪሎቻቸው ባይገኙም ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
4. የመኖሪያ ቤቱ ወይም ተሽከርካሪው ጨረታ አሸናፊ ለሆነው ተጫራች በማይክሮ ፋይናንሱ የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅደመ ሁኔታ መሠረት ብድር ሊመቻችለት ይችላል።
5. ከላይ በተራ ቁጥር 6 ላይ የተገለፀው የአሰላ ቅርንጫፍ አሰላ ከተማ፣ 05 ቀበሌ ባልቻ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ አሰላ ቅርንጫፍ ጨረታው የሚከናወን ሲሆን ቀሪዎቹ ሁሉም ጨረታዎች የሚከናወኑት በደ/ብርሃን ከተማ፣ እምዬ ምኒልክ ክ/ከተማ፣ ንግስት እሌኒ ቀበሌ አፄ ዘርዓያዕቆብ ህንጻ ላይ በሚገኘው የማይክሮ ፋይናንሱ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ አዳራሽ ውስጥ ይሆናል።
6. የተጫራቾች ምዝገባ ከእያንዳንዱ የንብረት ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል። በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም።
7. የሐራጁ አሸናፊ/ገዢ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ከፍያዎችን፤ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ የግብር ግዴታዎችን ገዥው/ አሸናፊው ይከፍላል።
8. ተጫራቾች የጨረታው ቀን ከመድረሱ 5 (አምስት) ቀን በፊት ከማይክሮ ፋይናንሱ ጋር በመነጋገር በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ በቦታው በመገኘት ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች መጎብኘት (መመልከት) ይቻላሉ።
9. ተጫራቹ የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅሑፍ ሲደርሰው ነው።
10. ማይክሮ ፋይናንሱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 637 6246 (ሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-09-07
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-09-07 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ/ማ
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Aug 04, 2026)
- Posted at: 2026-08-04T11:27:59.000Z