Uniforms and workwear

በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር በደብረታቦር ከተማ የሚገኘዉ የጎህ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተወሰነ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር በደብረታቦር ከተማ የሚገኘዉ የጎህ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተወሰነ 

  • የተለያዩ የደንብ ልብስ፣
  • የእንስሳት መድሃኒት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በሚከተለው መሰረት

  • ሎት 1. ብትን ጨርቅ የሀገር ውስጥ ታይዋን 308 ሜትር፣
  • ሎት 2. የሀገር ውስጥ ቱርክ ሸሚዝ ብዛት የወንድ 70፣ 3. የሴት ብዛት 4፣ ካፖርት የሱፍ ብሉ ብላክ ብዛት 5፣ ካኪ ቱታ ብዛት 92፣ ከጨርቅ የተሰራ ክብ ቆብ ብዛት 20፣ የሴት ጃኬት ብዛት 2 ፣
  • ሎት 3. የወንድ አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ በጥንድ ብዛት 82፣ የሴት አጭር ጉርድ ጫማ በጥንድ ብዛት 4 ፣የሳይት ጫማ በጥንድ ብዛት 2፣ የፕላስቲክ ቦት ጫማ 88 ፣
  • ሎት 4.ጎግል መነፅር ብዛት 10፣ የእጅ ጓንት ብዛት 34 ጥንድ፣
  • ሎት 6. የተለያዩ የእንስሳት መድሃኒቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት (ግለሰብ) መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟላ ተጫራች መወዳደር ይችላል፡-

  1. በዘርፉ የተሰማሩና የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. በእንስሳት መድሃኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን በማቅረብ የተሰማራ ከእንስሳት ኤጀንሲ የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (ዋስትና) ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በጎሕ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል (ሎት) የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚገዙ ዕቃዎችን አይነት፣ መጠንና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) የሚገልጽ የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከጎህ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ ቀርበው በመግዛት ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000561188126 ገቢ በማድረግ ኦርጅናል የባንክ አድቫይስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ የመወዳደሪያ ዋጋ፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን በሚያሳውቁት የቴሌግራም አድራሻ ማስላክ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-6 የተዘረዘሩትን ሰነዶች ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዬኑ ቢሮ በደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት በ3 ቀን ዉስጥ ያሸነፈበትን ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መዉስድ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. አሸናፊው የሚለየው በሎት (በምድብ) ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል ። ከሎት ውስጥ የአንዱን ዕቃ ዋጋ ካል ሞሉ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ።
  10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን እስከ 6.30 ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ10ኛው ቀን መጨረሻ ከቀኑ 8፡30 ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡40 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
  11. ዩኒዬኑ ከሚገዛው ዕቃ ውስጥ 20 በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው፡፡
  12. ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀብረት ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 ወይም 058 141 99 27 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ጎሕ ሁለገብ የገበ/ህ /ስ/ማህበራት ዩኒየን ኃ.የተወሰ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-13
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን እስከ 6.30 ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ10ኛው ቀን 8፡30
  • Bid opening: 2026-08-13 14:40
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን እስከ 6.30 ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ10ኛው ቀን 8፡40
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ጎሕ ሁለገብ የገበ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒየን ኃ.የተወሰነ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Aug 03, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T11:29:51.000Z
← Back to all tenders