Stationery and office consumables

የዶዶታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮክስ፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የቢሮ ዉስጥ ልዩ ልዩ አላቂ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች እና የሠራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2019

የዶዶታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በወረዳዉ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

  • ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣
  • ኤሌክትሮክስ፣
  •  የጽህፈት መሣሪያዎች፣
  •  የቢሮ ዉስጥ ልዩ ልዩ አላቂ ዕቃዎች፣
  • የጽዳት ዕቃዎች፣
  •  የመኪና ጎማዎች እና የሠራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ  ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax payer registration number) ያላቸው እና በፌዴራል፣ በክልል፣ በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የተሞላውን የጨረታ ሰነድ ዋናውና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮክስ፣ የጽፈት መሣሪያዎች፣ የቢሮ ዉስጥ ልዩ ልዩ አላቂ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች እና የሠራተኞች ደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በጽህፈት ቤቱ ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000039238695 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በጽህፈት ቤቱ የግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. በቀጣይ እለት ማለትም በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ የግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል፡፡
  5.  የመክፈቻው እለት በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተራ ቁጥር 4 በተጠቀሰዉ መሰረት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  6. ማንኛዉም ተጫራች ለእያንደንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000 (አስር) በአቅራቢያቸው በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (C.PO) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  7. አሸናፊው ተጫራች ያለ ምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ አስፈላጊ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና ዕቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ዴራ ከተማ ውስጥ በሚገኘዉ የወረዳዉ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች እስክርቢቶዎች፣ የፕሪንተር ቀለሞች እና ደንብ ልብስ ላይ የሚወዳደር ለሚወዳደርበት እቃ ናሙና (sample) ማቅረብ አለበት፡፡
  9. ተጫራቹ አሸናፊ ከሆነ ላሸነፈበት ዕቃ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መግባት ይጠበቅበታል፡፡ ዶዶታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አርሲ ዴራ ከተማ ከአዳማ በአሰላ መስመር 25 ኪ.ሜ

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር (0912311309)(0910379435) (0910022123 ይጠይቁ::

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአርሲ ዞን የዶዶታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-21 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Arsi Zone Dodota Woreda Finance and Econimic Development Bureau
  • Buyer address: የዶዶታ ወረዳ ገ/ት/ጽ/ቤት አርሲ ዴራ- ከአዳማ በአሰላ መንገድ 25 ኪሎ ሜትር፡፡
  • Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 04, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T12:26:53.000Z
← Back to all tenders