Stationery and office consumables
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 07 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 07 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችን በግዥ መለያ ቁጥር 01/2019 ማለትም
- ሎት 01 ደንብ ልብስ፣
- ሎት 02 አላቂ የቢሮ እቃዎች፤
- ሎት ዐ3 የፅዳት እቃ፤
- ሎት 04 የህትመት አገልግሎት፣
- ሎት 5 ቢሮ እቃዎች ጥገና አገልግሎት፣
- ሎት 6 የትራንስፖርት አገልግሎት፣
- ሎት 7 የጉልበትና ጭነት አውራጅ ጫኝ አገልግሎት እና
- ሎት 8 የዲኮር አገልግሎት በመጀመሪያ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ
- ለሎት 01 የጨረታ መስከበሪያ ብር 46,000 (አርባ ስድስት ሺህ ብር)፣
- ለሎት 02, 39,000(ሰላሳ ዘጠኝ ሽህ ብር)፣
- ለሎት 03. 46,000 (አርባ ስድስት ሽህ ብር)፣
- ለሎት 04. 10,500/አስር ሽህ አምስት መቶ ብር/
- ሎት 05. 17,000(አስራ ሰባት ሽህ ብር)፣
- ለሎት 06. 10,000(አስር ሽህ ብር)፣
- ለሎት 07. 10,000(አስር ሽ ብር፣
- ለሎት 8. 10,000/አስር ሺህ ብር/ በእያንዳንዱ ሎት
በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ ለየብቻ (CPO) ከኦርጅናል ጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።
- የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ላይ ማህተም ማድረግ አለባቸው። እንዲሁምፖስታዎች በእያንዳንዱ ሎት ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በላያቸው ላይ ማህተም መደረግ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነዱን ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 11፡30 ድረስ አየር ላይ ውሎ በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጨረታዉይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጊዜው ባለመገኘታቸው ጨረታውን አያስተጓጉለውም።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ኦርጅናል ሰነድ ላይ በእያንዳንዱ ሎት ላይ በማስገባት በግዥ ክፍል ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለሎት 01፤ ለሎት 2፤ ለሎት 3፤ ሎት 4 ናሙና ማቅረብ አለባቸው። እንዲሁም ለ ት 5፣6፣ 7፣ 8፣ በቀረበው ፍላጎት መግለጫ መሰረት ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ስርዝ ድልዝ የሆነ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት እስቶር ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ብቻ በባንክ በተረጋገጠ አሰርቶ መምጣት አለበት።
አድራሻ፡- በን/ስ/ላ/ክ/ከ ወረዳ 07 አስተዳደር ወደ ሳሪስ በሚወስደው መንገድ
ካድስኮ አዋሽ ባንክ ጀርባ 100 ሜትር ገባ ብሎ።
ለተጨማሪ መረጃ-
በሰልክ ቁጥር- 011 888 6532/ 011 888 5787 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ የወረዳ 07 አስተዳደር
Tender details
- Deadline: 2026-08-14
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 11፡30 ድረስ
- Bid opening: 2026-08-15 10:00
- Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Nifas Silk Lafto Sub City Woreda 07 FEDB
- Buyer address: ከጎተራ ወደ ሳሪስ በሚወስደው መንገድ ካዲስኮ ወረድ ብሎ ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ በስተጀርባ 100 ሜትር ገባ ብሎ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 04, 2026)
- Posted at: 2026-08-04T12:41:50.000Z