Stationery and office consumables

በአብክመ የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ገንዘብ መምሪያ የጽህፈት መሳሪያና ቋሚ አላቂ እና የጽዳት ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 03/2019 ዓ.ም

በአብክመ የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለዞን ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን

  1. የጽህፈት መሳሪያና ቋሚ አላቂ 
  2. የጽዳት ዕቃዎች

በግልጽ ጨረታ አውጥቶ በሎት ከአወዳዳረና አሸናፊውን ከተለየ በኃላ ከአሸናፊ ጋር ውል ገብቶ መግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  1. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የታደሰ መሆን አለበት፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርና የምስክር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢም መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ለጽህፈት መሳሪና ቋሚ አላቂ 50,000 ብር ለጽዳት ዕቃ 10,000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋረንት ወይም በገቢ መቀበያ ደረሰኝ በኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በምርጫቸው በአንዱ ከዋና/original/የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን 29/11/2018 ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እሰከ 15ኛው ቀን ማለትም 13/12/2018 ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ በኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 12 ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200/ ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋናውን ሰነድ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ከ29/11/2018 ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ማለትም እስከ 14/12/2018 ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን ገንዘብ መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡01 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሠዓት በግልጽ ይከፈታል። የመክፈቻ ዕለቱ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
  6. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው።

ስልክ ቁጥር 033 554 2119 ላይ በመደወል ማንኛውም መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፤ ካልሆነም በአካል ቀርቦ መረጃ መጠየቅ ይቻላል።

በአብክመ የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ገንዘብ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-20
  • Bid closing time: 10:01
  • Bid opening: 2026-08-20 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ANRS Oromo Nationality Zone Finance Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
  • Posted at: 2026-08-05T08:02:34.000Z
← Back to all tenders