Stationery and office consumables

የኦሞ ናዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው መ/ቤቶች የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሞ ናዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው መ/ቤቶች

  • የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ፣
  • እስቴሽነሪ፣
  • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
  • የተለያዩ ኮምፒተሮች /ላፕቶፖች እና ሶላሮች፣
  • የመንግስት ሠራተኞች ደንብ ልብስ፣
  • የጽዳት ዕቃዎች፣
  • የመኪና ጎማዎች የመኪና ዕቃ መለዋወጫዎች፣ እና
  • የሕንፃ መሣሪያዎች፣
  • ፈርኒቸሮች፣ እና የተለያዩ የሞተር ሳይክሎች በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት አወዳድረን ለመግዛት ስለምንፈልግ የሚከተለውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

1. የዘመኑን ንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ የመንግስት ግብር የከፈሉና መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ተፈላጊ መረጃቸውን ማቅረብ የሚችሉ።

3. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው ማስታወቂያው ከወጣበት እለት አንስቶ መሥሪያቤታችን ድረስ በመቅረብ ዘውትር በስራ ሰዓት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ወይም የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ቫትን ያካተተ ተሞልቶ መቅረብ አለበት፤ ካልሆነ ሰነዱ ውድቅ ይሆናል።

6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ) በባንክ በተረጋገጠ CPO በመሥሪያቤታችን ስም በማሰራት ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው።

7. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።

8. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ኦርጅናሉንና ኮፒው ላይ በእያንዳንዱ ገጾች የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በማኖር ማቅረብ አለባቸው ይህ ካልሆነ በሰነዱ ላይ ችግር ቢፈጠር መ/ቤቱ ተጠያቂ መሆን አይችልም።

9. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

10. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርግ ባቀረበው ናሙና መሰረት የማምጣት ግዴታ አለበት።

11. ናሙና ያላቀረበ ወይንም ፍቃደኛ ያልሆነ ከጨረታው ውጭ ይሆናል።

12. ክፍያ የሚፈፀመው ሙሉ በሙሉ በሞዴል 19 ተቆርጦበት ለባለ በጀት መሥሪያቤቶች ሲያስረክቡ እና የቀረበው ዕቃ ጥራቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።

13. ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በወቅቱ ማቅረብ ካልቻሉ ያስያዙት CPO ይወረሳል ተመላሽ አይሆንም።

14. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 21 (ሃያ አንድ የስራ ቀን) በመቆየት በ27/12/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከስራ ቀን ውጪ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

15. አሸናፊ የሆነ ድርጅት የአሸነፈበትን ዕቃዎች የማስጫኛ እና የማስወረጃ ወጪ እንዲሁም የትራንስፖርት ወጪ በራሱ ሸፍኖ ማቅረብ አለበት።

16. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0917016899

በኦሮ/ክል/መን/መስ/ በጅማ ዞን የኦሞ ናዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-02 10:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Omo Nada Woreda F/E/D/B
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር) ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሰነድ 500 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
  • Posted at: 2026-08-05T08:24:42.000Z
← Back to all tenders