Disposal, scrap and surplus sales

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 06/12/2018 እና 09/12/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

የጨረታ መስፈርቶች፡-

1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክሰ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣የዘመኑን ግብር የከፈለ ሰለ መሆኑ ክልራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክሰ እንቅሰቃሴያቸውን ለታክሰ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምሰክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።

2. ተጫረቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 06/12/2018 እና 09/12/2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።

3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (CPO) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ አንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጨራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እሰኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።

ተቁ

የጨረታ ቦታ

የጨረታው ዓይነት

ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች

የዕቃዎች መመልክቻ ቀን የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ

የጨረታ የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ቃሊቲ /// ቤት

ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ

ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ምግብ ነክ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት ኮስሞቲክስ መነፅር ጌጣ ጌጦች፣ ጠፍጣፋ ብረት ላሜራ የወዳደቁ ብረቶችና ፕላስቲኮች እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች

ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ 06/12/2018 09/12/2018 እስከ ጠዋቱ 345

ለግልጽ ጨረታ 06/12/2018 እና 09/12/2018 ዓም ከጠዋቱ 4:00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 06/12/2018 እና 09/12/2018 / 500 ሰዓት ይሆናል፡፡

5. የጨረታው መከፈቻ ቦታ- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፈ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የሰራ ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

7. ከአሸፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውሰጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖረበታል።

8. ከላይ በተቁ በተገለጹት ቀናት ውሰጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ያሰያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሸኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል።

9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-15
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-08-15 11:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Afar
  • Publishing entity: Awash Custom Commission Branch Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
  • Posted at: 2026-08-05T09:50:14.000Z
← Back to all tenders