Stationery and office consumables

በሸገር ከተማ አስተዳደር የእኔ ዲማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳ ውስጥ ላሉት ለመንግስት መ/ቤቶች ለ 2019 ዓም ለአንደኛ ዙር የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የመኪና ኪራይ፣ የመኪና እና ሞተር ሳይክል ጎማዎች፣ የግንባታ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የሆቴል ምግቦች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች የተለያዩ የህትመት ስራዎች እና ሞተር ሳይክል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2019

በሸገር ከተማ አስተዳደር የእኔ ዲማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳ ውስጥ ላሉት ለመንግስት መ/ቤቶች ለ 2019 ዓም ለአንደኛ ዙር የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የሰራተኞች ደንብ ልብስ፤ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት እቃዎች፡ የመኪና ከራይ፤ የመኪና እና ሞተር ሳይክል ጎማዎች፤ የግንባታ እቃዎች፤ ኤሌክትሮኒክስ፤ የሆቴል ምግቦች፤ ቋሚ የቢሮ እቃዎችየተለያዩ የህትመት ስራዎች እና ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛቹሀል።

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የ 2017 ዓም የከፈሉና የ2018 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ከ29/11/2018 ዓ.ም እስከ 19/12/2018 ዓ.ም ድረስ ለእያንዳንዱ ንግድ ዘርፍ ላይ የማይመለስ ብር 200 ሁለት መቶ ብር/ከፍለው ከገላን አራብሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ላለፉት ዓመታት ማለትም በ2017 ዓም እና በ2018 ዓም አንደኛ ዙር ግዢ ላይ በአቅራቢነት ችግር ያልፈጠሩ ጥሩ የአቅራቢነት ባህሪይ ያላቸው መሆኑን ከፌዴራል ወይም ከክልል ወይም ከከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዠ መ/ቤት የምስጋና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።

4. ማንኛውም ተጫራጮች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ንግድ ዘርፍ 0.5% ጠቅላላ ዋጋውን ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ ከጨረታው ሰንድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት።

6. ተጫራቾች የእቃዎቹን ዋጋ ዝርዝር የተጠየቀውን “Specification ሳይለውጡ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ላይ ዋጋው ከነ ተጨማሪ እሴት ታክስ በመሙላት ስማቸውን ፊርማችውንና አድራሻቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንታቸውን ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በማድረግ በአንድ ትልቁ ፖስታ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ 19/12/2018 ዓ.ም ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ጨረታው ከመዘጋቱ ከ10:00 ሰአት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በ20/12/2018 ዓ.ም በ 04፡00 ሰዓት ይከፈታል። ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይንም ወኪላቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግድውም።

8. የጨረታው ሳጥን ከታሸገ ወይንም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም

9. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ከውል ሰጪ መስሪያ ቤት ጋር በሚደረገው የውል ስምምነት መሰረት ገላን አራብሳ ለሚገኘው በውል ሰጪ ንብረት ከፍል ገቢ ያደርጋል።

10. መ/ቤታችን በሚያወዳድረው እቃዎች ብዛት ላይ እንደ አስፈላጊነቱ 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል።

11. ተጫራቾች እቃዎቹን አሸንፈው ለማቅረብ ሲዋዋሉ ካሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።

12. ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊ መሆናቸውን ከተገለጸ ከ 5 ቀን በኋላ በውል ሰጪ መስሪያ ቤት ድረስ በአካል በመገኘት የውል ስምምነት መፈጸም አለባቸው።

13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 21 48 79 85 / 09 11 44 03 17

በሸገር ከተማ አስተዳደር የእኔ ዲማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-25
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid opening: 2026-08-26 10:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: ሸገር ከተማ አስተዳደር የእኔ ዲማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Bid bond: 0.5% ለእያንዳንዱ ንግድ ዘርፍ
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ንግድ ዘርፍ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
  • Posted at: 2026-08-05T10:03:37.000Z
← Back to all tenders