Stationery and office consumables

በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2019 በጀት አመት አገልግሎት ላይ የሚውል እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ጨረታ ማስታወቂያ

በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2019 በጀት አመት አገልግሎት ላይ የሚውል

  • ሎት 1የጽህፈት መሳሪያ፣
  • ሎት 2. የጽዳት እቃ፣
  • ሎት 3. ቋሚ የቢሮ እቃ፣
  • ሎት 4 የተሸከርካሪ ጎማ፣
  • ሎት.5 የደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሰነዶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤

2. የንግድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት፣

4. ከገቢዎች ታክስ ክሊራንስ፣

5. በመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ፣

6. የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት ያለው፤

7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን እቃዎች ናሙና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO በየሎቱ 5000 ብር /አምስት ሺህ ብር/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 4 የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር / በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ቫአትን ጨምረው ዋናውና ፎቶ ኮፒውን ቴክኒካል ዶክመንት ለየብቻ ፋይናሻል ዶክመንት ለየብቻ በሰም በታሽገ ፖስታ በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾችና ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሪጅን ጽ/ቤቱ የሻይ ክበብ ውስጥ ይከፈታል። በ11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ከ11ኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

11. ጨረታው ጽንቶ የሚቆየው 60 ቀናት

ሪጅን ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ

ሐራቤ ዩኒቨርሲቲ ፍለፊት ከኢትፍሩት አጠገብ
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022 112 7165/022 11 195 9765 ደውለው የበለጠ መረጃ ማግኘት ይችለሉ።
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
የደቡብ ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት /አዳማ/


Tender details

  • Deadline: 2026-08-19
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-19 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Public Servants Social Security Administration
  • Bid bond: 5000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
  • Posted at: 2026-08-07T07:08:33.000Z
← Back to all tenders