Stationery and office consumables
በምሥራቅ ወለጋ ዞን የቦነያ ቦሼ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የጽ/መሳሪያዎች፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ የቢሮ ጽዳት ዕቃዎች፣ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግንባታ እቃዎች እና የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በምሥራቅ ወለጋ ዞን የቦነያ ቦሼ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለቦነያ ቦሼ ወረዳ መንግሥት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክቴር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉል የጽ/መሳሪያዎች፤ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፤ የቢሮ ጽዳት ዕቃዎች፤ ፈርኒቸር፤ ኤሌክትሮኒክስ፤ የግንባታ እቃዎች እና የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የፈልጋል።
ተፈላጊ መስፈርቶች
1. በዘርፉ ቀጥታ ንግድ ፈቃድ ያለውና የ 2018/19 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ ያሳደሰ እና ፎቶ ኮፒዉን ማቅረብ የሚችል።
2. የቫት እና የቲን መለያ ቁጥር ያለዉና ለእያንዳንዱ ፎቶ ኮፒዉን ማቅረብ የሚችል።
3. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበና ኮፒውን ማቅረብ የሚችል
4 . ከ20,000/ ሀያ ሺህ ብር በላይ ለሆነ ግዢ ዊዝሆልዲንግ (3%) ለመቁረጥ ፈቃደኛ የሆነ
5. ማንኛውም ተጫራች ማይክሮ ኢንተርፕራይዞችን ጨምሮ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር በቦነያ ቦሼ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ወይም በሲንቄ ባንክ የተረጋገጠ በቦነያ ቦሼ ገጽ ቤት ስም በማስያዝ ሲፒኦውን ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
6. ተጫራቾች የእቃዉን ዋጋ ከነ ተጨማሪ እሴት ታክስ በመሙላት ስማቸዉን፤ ፊርማቸዉን ና ማህተማቸውን በማድረግ ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒውን በተለያዬ ፖስታ በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል። በሰም አለመታሸጉ ከጨረታ ውጭ አያደርገውም።
7. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በተጠየቀ ጥራትና ብዛት መሠረት በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ ገቢ አድርጎ ክፍያዉን መቀበል አለበት።
8. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ1/12/18 ዓ.ም እሰከ 21/12/18 ዓ.ም ከ2፡30 አስከ 11፡30 ድረስ በቦነየ ቦሼ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 700/ ሰባት መቶ ብር /ብቻ በመክፈል ከቦነያ ቦሼ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዢ ክፍል ቁጥር 6 የጨረታ ሰነዱን መዉሰድ ይችላል።
9. የጨረታ ሳጥኑ በ21/12/18 11፡00 ታሽጎ በ22/12/18 ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የከፈታል።
10. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም።
11. መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-09 95 12 40 83/ 09 17 28 28 36/ 09 13 44 33 05
በምሥራቅ ወለጋ ዞን የቦነያ ቦሼ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-27
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-08-28 10:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: East Wollega Boneya Boshe Woreda FEDB
- Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 700.00 (ሰባት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
- Posted at: 2026-08-07T07:20:33.000Z