Stationery and office consumables
በቡኖ በደሌ ዞን የመኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት የሚውሉ ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በቡኖ በደሌ ዞን የመኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት የሚውሉ።
- የተለያዩ የፅሕፈት መሳሪያዎች እና የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች
- ኤሌክትሮኒክስ እና የፅዳት ዕቃዎች
- ጄነሬተሮች እና የተለያዩ ሞዴሎች ያላቸው ሞተር ሳይክሎች
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ
- የመኪናና የሞተር ሳይክሎች ጎማ ከነ ካለማዳሪያዎቻቸው
- የስፖርት ዕቃዎችና አልባሳት
- የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ መሳሪያዎች
- የተለያዩ የግንባታ መሣሪያዎች ለንግድ ሥራ የሚውሉ ማሽነሪዎች እና ሌሎች መሣሪያዎችን በወረዳው ለሚገኙ መንግስት መ/ቤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለመኮናተር ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ።
1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ኖሮት የታደሰ ማስረጃ ማቅረብና የዘመኑን ግብር የከፈለ።
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት አቅራቢነት ዝርዝር የተዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ።
3 የሚያሸንፉበት የዕቃ ዋጋ ከብር 10,000 በላይ ከሆነ 3% ዊዝሆልዲንግ መክፈል የሚችል።
4. ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ በጥሬ ገንዘብ ብር 30,000 (ሠላሣ ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችል።
5. ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% ማስያዝ የሚችል።
6. ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ ዕቃዎቹን በራሱ ወጪ እስከ መኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መጋዘን ማቅረብ የሚችል
7. ጥራት የሌላቸው ዕቃዎችን ለመመለስ ፈቃደኛ የሆነ።
8. በድርጅቱ ስም የተዘጋጀ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችልና የቲን ቁጥር(TIN)መኖሩን ማረጋገጫ የሚያቀርብ።
9. መ/ቤቱ ለሚጠራጠራቸውና ማጣራት ለሚፈልጋቸው ዕቃ ናሙና ማቅረብ የሚችል።
10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/አሥራ አምስት/የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን በ11:00 ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን በሚቀጥለው ቀን በ3:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
11. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ በ 500(አምስት መቶ ብር) ከመኮ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በመግዛት ዋጋቸውን ሞልተው ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ።
12. ማሳሰቢያ: መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 17 99 22 82 ይደውሉ።
የመኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-25
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/አሥራ አምስት/የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን በ11:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-26 09:30
- Bid opening (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/አሥራ አምስት/የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን በ11:00 ሰዓት የሚጠናቀቅ ሲሆን በሚቀጥለው ቀን በ3:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Buno Bedele Zone Meko Woreda FEDB
- Bid bond: ለእያንዳንዱ 30,000 (ሠላሣ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
- Posted at: 2026-08-07T07:49:44.000Z