Stationery and office consumables

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በ2019 በጀት አመት ለወረዳው ጽ/ቤቶች አገልግሎት መስፈርቱን የሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/1030/2018

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በ2019 በጀት አመት ለወረዳው ጽ/ቤቶች አገልግሎት መስፈርቱን የሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት

  • ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ
  • ሎት 2 የፅዳት ዕቃ
  • ሎት 3 ደንብ ልብስ
  • ሎት 4 ኤሌክትሪክ ዕቃ
  • ሎት 5 የአትክልት ዘር
  • ሎት 6 የእንስሳት ጤና መድሃኒት
  • ሎት 7 የመኪና ጎማ
  • ሎት 8 የሞንታርቦ ከነጀነሬተር እና መድረክ ዲኮር እና VIP ዲኮር ኪራይ
  • ሎት 9 ድንኳን አገልግሎት ኪራይ
  • ሎት 10 የመስተንግዶ አገልግሎት
  • ሎት 11 የሰራተኞች ካፌ አገልግሎት
  • ሎት 12 የህትመት አገልግሎት
  • ሎት 13 የህዝብ ማመላለሻ ሀይገር/ መኪና ኪራይ
  • ሎት 14 የሚንባስ መኪና ኪራይ

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ይፈልጋል።

1. ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-14 ለተጠቀሱት እቃዎች አግባብነት ያለው ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድ እና የምዝገባ ወረቀት ኮፒ በገቢዎች የጨረታ መሳተፊያ ጊዜ የሚገልፅ ደብዳቤ ያለው በአቅራቢነት የተመዘገቡ እንዲሁም 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በላይ ዕቃ የሚያቀርቡ ድርጅቶች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት አስኮ ኖክ ማደያ : አለፍ ብሎ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ በመገኘት ለአያንዳንዱ ሰነድ 300 ብር (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ትችላላችሁ።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 0.5-2 % ካለው ውስጥ (1%)ቱን ያለውን የእቃውን ወደ ብር ተቀይሮ እያንዳንዱ ዋጋ

  • በሎት 1 1% 12000
  • ለሎ2 1% 12000
  • ለሎት 3 1% 12000
  • ለሎት4 1% 8000
  • ለሎት 5 1% 6000
  • ለሎት6 1% 6000
  • ለሎት 1 7 1% 10000
  • ሎት 8 1% 8000
  • ሎት 9 1% 8000
  •  ለሎት 10 1% 8000
  • ለሎት11 1% 8000
  • ሎት 12 1% 8000
  • ሎት 13 1% 8000
  • ሎት 14 1% 8000 በባንክ በተረጋገጠ (Cpo)ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በፖስታ በማድረግ ጨረታው በአየር እስከ ዋለበት የመጨረሻ ቀን ድረስ እስከ ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. ተጫራቾች የአያንዳንዱ እቃ የሚሸጡበት ዋጋ በመግለፅ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሙሉ አድራሻውን ስማቸውንና የጨረታ አይነት በመጥቀስ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የተጠቀሱት እቃዎች ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል መጫረት ይችላሉ።

6. የጨረታው ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን ጨረታው በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል።

7. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ፋይናንስ 1ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።

8. ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ በ4/አራት/ፖስታ በማሸግና በግልፅ በመፃፍ ኦርጂናል ቴክኒካልና ፋይናንሻል እንዲሁም ቴክኒካልና ፋይናንሻል ፎቶ ኮፒ ማቅረብይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆን አለበት።

10. ወረዳው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ተጫራቾች ሳምፕል ስታመጡ ለጋራ ደህንነት ሲባል በማይበጣጠስ ወይም በማዳበሪያ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ4 ፋይናንስ ጽ/ቤት አስኮ ኖክ ማደያ አለፍ ብሎ ስልክ

ቁጥር /09-84-659144

ማሳሰቢያ፡- እያንዳንዱ ሰነድ በየሎቱ በተለያዩ ፖስታ ተሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡ እንዲሁም ጨረታው ከመታሸጉ በፊት የጨረታ ሰነዱንና ሳንፕሎችን መቅረብ አለባቸው፡፡ ከጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ በሚያመርቱት ምርት እና ካደራጃቸው አካል በሚቀርበው ህጋዊ ድጋፍ በንግድ ዘርፉ በተሰማሩበት (በሚቀርበው ድጋፍ ደብዳቤ መሠረት) ይስተናገዳሉ።

 በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-19
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-19 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ketema Sub City Woreda 14 Finance Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሰነድ 300 ብር (ሦስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
  • Posted at: 2026-08-07T07:55:56.000Z
← Back to all tenders