Stationery and office consumables
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የኮምቦልቻ ወረዳ ፍርድ ቤት ለስራ የሚውሉ የተለያዩ ቋሚ እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የኮምቦልቻ ወረዳ ፍርድ ቤት ለስራ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ መግዛትን ይመለከታል፣ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃዎች ማቅረብ የሚችሉትን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- የተለያዩ ቋሚ እቃዎች
የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የመኪና እቃናጎማዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡ ተወዳዳሪዎች ማቅረብ ያለባቸው።
1. በዘርፉ የተሰማሩበትን ስራ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ከፍለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የምትወዳደሩበትን የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ብር 25000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ብር በቢሮ ስም አስገብቶ ማቅረብ የሚችል።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. የግብር ከፋዮች ቁጥር ቲን ያላቸው እሴት ታክስ 15 ፐርሰንት ቫት ተመዝጋቢዎች መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች ጨረታ ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወደ ኮምቦልቻ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ ገቢ ማድረግ የሚችል።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከኮምቦልቻ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ መግዛት ይችላል።
7. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናትአየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የበለጠ መረጃ፡- ለማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0913893337 / 0937503917 /0913746418/ 095403523 ደውለው ወይም መ/ቤታችን ድረስ በጽሁፍም ሆነ በአካልቀርበው መረዳት ይችላሉ።
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የኮምቦልቻ ወረዳ ፍርድ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-25
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-25 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: East Harage Zone Kombolcha Woreda Court
- Bid bond: 25,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
- Posted at: 2026-08-07T08:06:41.000Z