Stationery and office consumables

በምዕ/ሐረርጌ ዞን የሸነን ዱጎ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም የቢሮ መገልገያ እቃዎች ማለትም የኤሌክትሮኒክስ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች እና የደንብ ልብስ እንዲሁም የግንባታ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በምዕ/ሐረርጌ ዞን የሸነን ዱጎ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም የቢሮ መገልገያ እቃዎች ማለትም የኤሌክትሮኒክስ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች እና የደንብ ልብስ እንዲሁም የግንባታ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የተቀመጡ መስፈርቶች

1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈሉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ Vat (የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የ2019ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።

2. ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች የወረዳው መጋዘን ድረስ ትራንስፖርት ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የመልካም ስራ አፈፃፀም ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተመሳሳይ የእቃ አቅርቦት የሶስት (3) እና ከዛ በላይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርበታል።

4. ተወደዳሪው በዝርዝር ለመንግስት ተቋማት የሚያቀርበውን እቃ ማስረጃ ማቅረብ አለበት።

5. የእቃውን ዝርዝር ሙሉ የጨረታ መመሪያ የያዘው ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀን ከወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር አምስት መቶ (500) ብር ከፍሎ መግዛት ይኖርበታል።

6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ ሃያ ሺህ (20,000) ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል።

7. ጨረታው የሚከፈተው ጋዜጣው በወጣ በአስራ አምስት (15)ቀን የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ስምንት ሰዓት (8፡00) ተዘግቶ ስምንት ሰዓት ተኩል (8፡30) ተወዳዳሪዎቹ ወይም ህጋዊ ወኪል ባሉበት በግልጽ ይከፈታል።

8. በዚህ ጨረታ ማይክሮዎች ይበረታታሉ፡፡መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 0920693941/0915088335

በምዕ/ሐረርጌ ዞን የሸነን ዱጎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-24
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15)ቀን የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ስምንት ሰዓት (8፡00) ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-24 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15)ቀን የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ስምንት ሰዓት (8፡30) ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Shenen Dugo Woreda Finance Office
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
  • Posted at: 2026-08-07T08:12:05.000Z
← Back to all tenders