Audio-visual, photography and graphic design
ያገለገሉ የቤት ቁሳቁሶች የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አብይ ሰይፉ ወ/ጊዮርጊስ እና በፍ/ባለዕዳ አይዳ ደስታ ገ/መድህን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.85538 በቀን 27/06/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ እና በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.102296 በቀን 14/09/2017 ዓ.ም በኮ/መ/ቁ.102296 በቀን 12/08/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር BM-5/005 ውስጥ የሚገኙ ፍ/ያረፈባቸው ያገለገሉ የቤት ቁሳቁሶች ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 413,600 (አራት መቶ አስራ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ9፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተአሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-24
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-08-24 15:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
- Posted at: 2026-08-07T08:36:06.000Z