Stationery and office consumables
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ጉጂ ዞን የአባያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃችን፣ ፈርኒቸሮችን፣ የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች (construction materials)፣ የመኪና ጎማዎችን፣ ትልቁ ሞንታርቦ (full sound system)፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ እና
Description
ለመጀመሪያ ግዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ጉጂ ዞን የአባያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃችን፣ ፈርኒቸሮችን፣ የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች (construction materials) ፣ የመኪና ጎማዎችን፣ ትልቁ ሞንታርቦ (full sound system) ፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ እና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዕቃዎች አስፈላጊውን መስፈርት የሚያሟሉትን ተጫራቾ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የመወዳደሪያ መስፈርቶች፡-
1. በንግድ ዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለውና በዘመኑ የታደሰበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
2. ተጨማሪ አሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነና የንግድ ሥራ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው
3. ተጫራቾች የዕቃውን ዋጋ በሚሞላበት ወቅት የዕቃውን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ(Brand Name and specification) በግልጽ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
4. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የሚቀርብ ጨረታ ከበቂ መግለጫዎቹ (specification) ጋር መሆን አለበት።
5. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ/ ድርጅት የጽህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎች፣ የሠራተኛች የደንብ ልብስና የጫማዎች ናሙና (Sample) ማቅረብ ይጠበቅበታል።
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የዕቃዎቹን ማጓጓዣ ወጪ ያካተተ መሆን አለበት።
7. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ማቅረብ ይኖርበታል።
8. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጀምሮ እስከ 14ኛው የሥራ ቀን ድረስ ተፈላጊ የመወራደሪያ ዶክመንቶች ዋናውንና የማይመለስ አንዳንድ ኮፒዎችን በኤንቨሎፕ የታሸገ በመያዝ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከአባያ ወረዳ የገቢዎች ባለሥልጣን ቅ/ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በ15ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ስዓት ላይ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ በዕለቱ ተራቾች ወይም ህጋዊ ወሎቻቸው በተገኙበት 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
10 መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ከማንኛውም ተጫራች ከቫት 7.5% (ፐርሰንት) ለመንግስት የሚቀነስ ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡-
- ዕቃዎችን በማጓጓዝ ሂደት ላይ ለሚደርስ ማንኛውም ብልሽት መ/ቤታችን ኃላፊነቱን አይወስድም፣
- የጨረታ ማወዳደሪያ ቀን ቅዳሜና ዕሁድና በዓል ላይ የሚውል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ዕለት ላይ ይሆናል።
- መ/ቤታችን ከዲላ ከተማ በስተ ደቡብ በኩል 5 ኪ.ሜ ርቀት በአስፓልት መንገድ ላይ ይገኛል፤
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09-11-77-21-36 / 09-16-62-62-32 መደወል ይችላሉ።
በምዕራብ ጉጂ ዞን የአባያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-24
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-24 14:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የሥራ ቀን 8፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Abaya Woreda FEDB
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
- Posted at: 2026-08-07T08:44:48.000Z