Stationery and office consumables

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአለታ ወንዶ ከተማ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አላቂ የቢሮ የጽህፈት መሳሪያዎችን በጨረታ ዋጋ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአለታ ወንዶ ከተማ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አላቂ የቢሮ የጽህፈት መሳሪያዎችን በጨረታ ዋጋ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ተጫራቾች

  • አግባብነት ያለው ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው/ያላት ኦረጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና የዘመኑን ወይም ለ2018/2019 ዓ.ም ግብር የገበሩበት ማረጋገጫ ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
  • የ2018/2019 ዓ.ም የግብር ከሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።
  • የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ ያላት ኦረጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
  • ጊዜው ያላለፈበት በአቅራቢነት በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከመንግሥት መ/ቤት የተሰጠ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያለው/ያላት ኦረጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
  • የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 30,000 ከታወቀ ባንክ (CPO) ማስያዝ የሚችል
  • የውል አፈፃፀም ዋስትና ማስከበሪያ ከሚያቀርበው ጠቅላላ 10% በጥሬ ወይንም ከታወቀ ባንከ የተሰጠ (CPO) ማስያዝ የሚችል
  • ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው
  • በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ያቀረቡት ናሙና ወዲያው ተመላሽ ይደረጋል።
  • ማንኛውም ወጪዎች ማለትም የጉምሩክ የትራንስፖርት የባንክ እና የሌሎችም አገልግሎት ወጪዎችን በራሱ ሸፍኖ ዕቃውን ማስረከብ የሚችል
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ ለአ/ወ/ከ/ገ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል እና ሰነዱን ከአ/ወ/ከ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ሥራ ሂደት በሮ ቁጥር 08 በመውሰድ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነዱ ላይ የአንዱን ዋጋ ብቻ በመሙላት ቴክኒካል ዶክመንት እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እንዲሁም ሁለት ሁለት ፎቶ ኮፒው ለየብቻ በማድረግ በአንድ ፖስታ አሽጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአ/ወ/ከ/ፋ/ኢ/ልጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገበት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሳጥን በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒና ማመልከቻ ማቅረብ ይርባቸዋል።
  • መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  • አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ሌላው ተጫራች ተንተርሶ መጫረት አይችልም
  • የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውመ ከቀረበም የዋጋ ትንታኔ መያያዝ አለበት
  • ጨረታው መክፈቻ በሥራ ቀን ካዋለበት ቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይሆናል
  • ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ 046 224 0152 እና 046 224 0627 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአለታ ወንዶ ከተማ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-28
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-28 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Aleta Wondo City Administration Finance and Economic Development Office
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
  • Posted at: 2026-08-07T08:47:42.000Z
← Back to all tenders