Stationery and office consumables

በማ/ኢ/ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት በ2019 በጀት አመት የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ጌ/ወ/ፋ/ ግ/ጨ/መ/ቁ/01/2019

በማ/ኢ/ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት በ2019 በጀት አመት በተፈቀደው መደበኛና ካፒታል በጀት በወረዳችን የሚገኙ አጠቃላይ ሴክተር መ/ቤቶች እና የቋንጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል በመሆኑም ወረዳው የሚፈልጋቸው እቃዎች እንደሚከተለው በሎት ተከፋፍለው ቀርበዋል::

  • ሎት 1 እስቴሽነሪ 
  • ሎት-2 ኤሌክትሮኒክስ
  • ሎት-3 ጀነሬተር
  • ሎት 4 የጽዳት እቃዎች
  • ሎት 5 የደንብ ልብሶች
  • ሎት-6 ሞተር ሳይክል ጎማና ኮመነዳሪዎች
  • ሎት 7 ሞተር ሳይክሎች
  • ሎት 8 የመኪና ጎማዎች
  • ሎት-9 የፈርኒቸር እቃዎች
  • ሎት 10 የህንጻ መሳሪያዎች
  • ሎት-11 የውሃ እቃዎች ሲሆኑ ይህ ጨረታ ግዥው ተግባራዊ የሚሆነው በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ባወጣው መደበኛ የጨረታ ሰነድ መሰረት ሆኖ የጨረታው ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት በሙሉ የምታሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡-

1. የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ አቅራቢዎች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በጣት አሻራ ላይ የተመሰረተ እና የተረጋገጠ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡

2. ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የመክፈል ግዴታቸው የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተሰጠ ማስረጃና የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ንግድ ፈቃድ ምዝገባ በሚወዳደሩበት ዘርፍ(ሎት) ጋር አንድ የሆነ ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾቾ በእቃ አቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት በኦንላይን ብቻ የተመዘገቡ እና ስለ መመዝገባቸው የሚገልጽ መረጃ /e-GP /Electronic Government procurement ማቅረብ ይኖርባችኋል።

4.የበጀት አመቱ ከግብር ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ(የምስክር ወረቀት) ማቅረብ የምትችሉ(Tax Clearance)

5. በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የምስክር ማስረጃ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው::

6. አሸናፊ ተጫራች ለግዥ ፈጻሚ የሚሰጠው ደረሰኝ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ ከሆነ (Q.R) ደረሰኝ መሆን አለበት::

7. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾቾ ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል።

8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ የእቃ ብራንድ፤ የስሪት ዘመን፤ ሞዴል፤ የተመረተበት ሀገር እና ሌሎች ስለ እቃው መጠቀስ ያለበትን ነገር መገለፅ አለባቸው::

9. እያንዳንዱ ተወዳዳሪ የእቃዎች ዋጋ ሲሞላ ቫት ጨምሮ መሆን አለበት ካልጨመሩ እንደ ጨመሩ ታሳቢ ይደረጋል።

10. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይንም ከጨረታ እራስን ማግለል አይቻልም::

11. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው።

12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በመግቢያው ከተገለጹት ከሎት1-11 በተዘረዘሩ የቋሚ እና አላቂ እቃዎች ሎት 3 እና 4 10,000 /አስር ሺህ/ ብር የተቀሩት ሎቶች እያንዳንዳቸው 15,000 /አስራ አምስት ሺህ/ ብር ለፋይናንስ ጽ/ቤት CPO ሲፒኦ (በካሽ) ወይም ከመድን ድርጅቶች የሚቀርብ ዋስትና በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ቦንድ በጌታ ወረዳ ፋይናንስ ስም እውቅና ባለው ባንክ ህጋዊ ሲፒኦ ማሰራት አለባቸው ለቋንጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ደግሞ ከሎት 1-5 እና ሎት 9 ለተዘረዘሩት እቃዎች በእያንዳንዱ ሎት 5000 (አምስት ሺህ ብር) ሲፒኦ ወይም በካሽ በቋንጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስም በማሰራት ማስያዝ አለባቸው። 

13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ በግልጽ ጽሁፍ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት። 

14. ተጫራቾች በአንድ እናት ፖስታ የእያንዳንዱን ሎት ሲፒኦ በማካተት በጥንቃቄ ታሽጎ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ (ቅጂ) ሰነድ በድርጅቱ ባለስልጣን የተፈረመበት እና በእያንዳንዱ ገጽ ማህተም የተደረገበት ሆኖ እስከ ጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ 06 በመምጣት ለፋይናንስ እና ለቋንጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ብሎ በመለየት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ በሳጥኑ መጨመር አለባቸው።

15. በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የስራ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ ጌታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር ለፋይናንስ ጽ/ቤት 200 ብር/ሁለት መቶ/ ለቋንጤ የመ/ደ/ሆስፒታል በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይቻላል።

16. የጨረታ ሳጥኑ 15ኛው /አስራ አምስተኛ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 8፡00 ሰዓት በጨረታው ኮሚቴ ታሽጎ በዛው እለት 8፡30 ተጫራቾች |ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል /ባይገኙም ይከፈታል።

17. መ/ቤታችን የሚፈልጋቸው ጥራታቸው የጠበቁ የተለያዩ የቢሮ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ እና ቋሚ እቃዎች ሲሆኑ ግዢ የምንፈጽምባቸው እቃዎች የምንረከበው በጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መጋዘን እና በቋንጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መጋዘን ይሆናል።

18. አሸናፊ ከተለየ ውል ከተገባ በኋላ ግዢ የምንፈጽምባቸው እቃዎች መረከቢያ ጊዜ ገዢው ከታዘዘበት ቀን ጀምሮ ባሉ 25 ቀናት ውስጥ ይሆናል።

19. ግዥ ፈጻሚ አካል አሸናፊ ከተለየ በኋላ በሚገዛቸው ጥራታቸው የጠበቁ የተለያዩ የቢሮ አገልገሎት የሚውሉ አላቂ እና ቋሚ እቃዎች 20% ፐርሰንት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት ይኖረዋል።

20. የቀረበው የመወዳደሪያ ሃሳብ (ዋጋ ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምር ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት።

21. በሁሉም ዘርፍ የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ለእቃዎቹ ናሙና ሳምፕል ሲጠየቅ ማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል።

22. በጨረታ ማስታወቂያና በጨረታ ሰነዱ መሃከል ልዩነት ከተፈጠረ የጨረታ ሰነዱ የበላይነት ይኖረዋል።

23. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ለግዥ ፈጻሚ አካል ማቅረብ የሚችሉት ጨረታው ከመክፈቻ 5 ቀናት በፊት በጽሁፍ መሆን አለበት፡፡

24. ተጫራቾች የጨረታው የመወዳደሪያ ሃሳብ ማቅረቢያ ቋንቋው በአማርኛ/በእንግሊዝኛ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡-

1. ግዢ ፈጻሚው አካል ጨረታው በሙሉ /በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።

2. አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ በ7ተኛው ቀን 10% ባሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት።

3. የቫት 7.5% የምንቆርጥ መሆኑንና

4. የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 መሰረት ዊዝ ሆልድ 3% የምንቆርጥ መሆኑን አናሳስባለን።

5. ከዚህ በፊት በወረዳችን ተወዳድረው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው እቃ ያላቀረቡ ተጫራቾች እና በክልሉና በዞኑ የታገዱ ተጫራቾች መወዳደር አይችሉም።

6. ሁለት ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዋጋ እኩል ከሆነ አብዛኛው እቃ ላሸነፈ ተጫራች የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ 0967 441 304/0921 385 494/0913 205 760
አዲስ አበባ ሰነድ የሚሸጡ ስልክ ቁጥር 0973 757 244/09611  78 110/0910 698 858
በማ/ኢ/ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-22
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ 15ኛው /አስራ አምስተኛ/ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-22 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ 15ኛው /አስራ አምስተኛ/ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 8፡30 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: ጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500 (አምስት መቶ) ብር ለፋይናንስ ጽ/ቤት፣ 200 ብር/ሁለት መቶ/ ለቋንጤ የመ/ደ/ሆስፒታል
  • Published on: Addis Zemen (Aug 08, 2026)
  • Posted at: 2026-08-08T07:41:49.000Z
← Back to all tenders