Stationery
በጉ/ክ/ከ/ወ/9/ፋ/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ስራ ሂደት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎች እና አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ከአሸናፊዎች ጋር አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር፡-001/2018 ዓ.ም.
በጉ/ክ/ከ/ወ/9/ፋ/ፅ/ቤት የመንግስት ግዥ ስራ ሂደት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ግዥዎች በ2019 በጀት ዓመት
- ሎት1. የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት2. የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት3. የደንብ ልብስ እና ስፌት
- ሎት4. የተለያዩ ህትመቶች
- ሎት5. የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት6. የተለያዩ መስተንግዶ
- ሎት7. የኤሌክትሮኒክ እቃዎች ጥገና
- ሎት8. ትራንስፖርት አገልግሎት
- ሎት9. የተለያዩ አገልግሎት ዲኮር,
- ሎት10. ቋሚ እቃዎች
በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ከአሸናፊዎች ጋር አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተለውን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በተጨማሪም ታክስ (VAT) ከፋይ መሆኑን የሚያረጋገጥ ወረቀት እና ቲን ነምበር ያላቸው።
- በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ያለባቸውን እቃዎች ላይ ናሙና ማቅረብ የሚችሉ።
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው በተሰጠበት የንግድ ዘርፍ ብቻ መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በስሙ የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው።
|
ሎት ቁጥር |
የሎት ዝርዝር |
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር ሲፒኦ |
ምርመራ |
|
1 |
የጽህፈት መሳሪያ |
60,000 |
|
|
2 |
የጽዳት ዕቃዎች |
82,500 |
|
|
3 |
የደንብ ልብስ እና ስፌት |
51,000 |
|
|
4 |
የተለያዩ ህትመቶች |
16,500 |
|
|
5 |
የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ |
18,000 |
|
|
6 |
የተለያዩ መስተንግዶ |
61,962 |
|
|
7 |
የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና |
10,438 |
|
|
8 |
ትራንስፖርት አገልግሎት |
55,302 |
|
|
9 |
የተለያዩ አገልግሎት ዲኮር |
18,075 |
|
|
10 |
ቋሚ እቃዎች |
30,000 |
|
6. በጨረታው ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
7. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚውል ሲሆን ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) የኢትዮጵያ ብር በመክፈል የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ ቤት ቢሮ ቁጥር 003 ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ በተዘጋጀው በአንድ ኮፒ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
9. በጥቃቅን አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ አካላት ባመረቱት ምርት ላይ መወዳደር ከፈለጉ በጽ/ቤት ኃላፊ ተፈርሞ የመጣ ማስረጃ ሲያቀርቡ ሰነድ ወስደው መወዳደር ይችላሉ።
10. በስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው ማስረጃ በማቅረብ የሚወዳደሩ ድርጅቶች የጨረታ ሰነድ ብቻ በነጻ የሚሰጥ ሲሆን ከላይ ለተዘረዘሩት የጨረታ ሎቶች ሲፒኦ ማስያዝ ግድ ነው ሲፒኦ ያላቀረቡ ተጫራቾች ከውድድር ውጪጪ ይሆናሉ።
11. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር ዐዐ3 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
12. ጨረታው በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን 3፡00 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 003 የሚከፈት ሲሆን ባይገኙም ከመከፈት የሚያግደው የለም።
13. ጽ/ቤቱ ከውል በፊት የእቃውን ብዛት 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ ከውል ቦኋላ የነጠላ ዋጋ 25% የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. አሸናፊዎች ውል እንዲገቡ በደብዳቤ ከተነገራቸው ቀን አንስቶ በአምስት ተካታታይ ቀናት ውስጥ የውሉን 10% ሲፒኦ በማስያዝ ውል መግባት ይኖርባቸዋል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ውል ገብቶ በውሉ መሰረት መፈፀም ያልቻለ ያስያዘው ሲፒኦ ተወርሶ ለደረሰው በደል በመመሪያ መሰረት ተጠያቂ ይሆናል።
15. አንዱ በአንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
16. እያንዳንዱ ተጫረቶች ለሚያስገባው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት።
17. ተጫራች የአንዱ ነጠላ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጠቀስ አለበት ።ያልተጠቀሰ ከሆነ ቫት እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
18. አሸናፈው ያሸነፈባቸውን ንብረቶች የወረዳው ንብረት ክፍል ድረስ አምጥተው ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
19.ፖስታዎች መታሽግና በላያቸው ላይ ማህተም መደረግ ይኖርባቸዋል።
20. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
21. አድራሻችን ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ዐዐ3 እንቁላል ፋብሪካ በእምቢልታ ሆቴል ከታደሰ ብሩ ት/ቤት 300ሜ ከፍ ብሎ ደምቦባ ህንፃ አካባብ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112595309 መደወል ይቻላሉ።
በጉ/ክ/ከ/ወ/9/ፋ/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ስራ ሂደት
Tender details
- Deadline: 2026-08-19
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-20 09:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 3፡00 ሰአት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Gulele Sub CIty Woreda 9 FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 250.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 08, 2026)
- Posted at: 2026-08-08T08:11:54.000Z