Stationery and office consumables

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የቢሮ እቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር AMFI 01/2019

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የቢሮ እቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ምድብ 1፦ ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር እና ተያያዥ ዕቃዎች ግዥ
  • ምድብ 2፦ የጽሕፈት መሣሪያዎች እና ተያያዥ ዕቃዎች ግዥ
  • ምድብ 3፡- የፈርኒቸር እና ተያያዥ ዕቃዎች ግዥ

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፦

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑን የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለምድብ 1 የሚቀርብ 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) እና ለምድብ 2 እና 3 የሚቀርብ ለእያንዳንዳቸው 350,000.00 (ሦስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና በአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ስም አሠርተው እንደምርጫቸው በአንዱ ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 (አሥራ አንድ ሰዓት) ድረስ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በአሐዱ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 0003230410101 ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000505229014 ገቢ በማድረግ ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ አቅርበው ከአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ወሰን ቅርንጫፍ መውሰድ ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዙ ሰነዶች የዋጋ ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን ሲሆን ለምድብ 1 ከጠዋቱ 3፡00 (ሦስት ሰዓት) ድረስ ለምድብ 2 ከቀኑ 5፡00 (አምስት ሰዓት) ድረስ እና ለምድብ 3 ከቀኑ 8፡00 (ስምንት ሰዓት) ድረስ ብቻ ከአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ወሰን ቅርንጫፍ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::

4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ምድብ 1 ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ፣ ምድብ 2 ከረፋዱ 5፡00 ሰአት ታሽጎ በእለቱ ከረፋዱ 5፡30 ላይ እና ምድብ 3 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ከቀኑ 8፡30 ላይ በግልጽ ተከፍቶ የእቃው ዋጋ ተጫራቾችና ታዛቢዎች ባሉበት ይነበባል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም ብሔራዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡ /ትክክለኛው የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል፡፡

5. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው አግባብ በራሳቸው ሙሉ ወጪ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ዋና መ/ቤት (ደብረ ብርሃን አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ሕንጻ) ድረስ አምጥተው ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡

7. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በተቋሙ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ እና በደብዳቤ እንገልፃለን፡፡

8 ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 0116 376 668 / 0116 376 457 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-18
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-08-18 14:30
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ/ማ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 08, 2026)
  • Posted at: 2026-08-08T08:15:24.000Z
← Back to all tenders