Disposal, scrap and surplus sales

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ

  • ያገለገሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣
  • በስክራኘ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች፣
  • ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣
  •  DCI፣
  • የተለያዩ ንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ከነመዳሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ የህክምና እቅዎች፣ በርሜሎች፣ በርሜሎች ከነክዳናቸው ጀኔሬተሮች ቦቴ

ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች ከአፍንጮ በር ወደ 6 ኪሎ በሚወስደው መንገድ ፍቅር ኘላዛ ህንፃ ላይ በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመምጣት የተለያዩ ተቋማት ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች፣ በስክራኘ መልክ የሚወገዱ ተሸከርካሪዎች እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ለእያንዳንዳቸው ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር)፣ እንዲሁም የተለያዩ የአገለገሉ የንብረቶች (የተሸከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ጀኔረተሮች፣ የህክምና እቃዎች፣ ከነመዳሪዎች፣ በርሜሎች፣ በርሜሎች ከነክዳናቸው ቦቴ ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ተገኝተው መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት ሰዓት ድረስ ተጫራቶች ሰነድን ማስገባት ይችላሉ ፡፡
  3. ተጫራቾች በአሃዝና በፊደል እንዲሁም በነጠላና በጥቅል በሰጡት ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ አገልገሎቱ ከፍተኛውን ዋጋ ወስዶ ያወዳድራል፡፡
  4. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለጽ በመጫረቻ ሠነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በአንድ መለያ ቁጥር(መደብ) ስር ያለውን ንብረት ብዛት በሙሉ መጫረት አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ለሸያጭ የተዘጋጁትን የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ቸርኬዎች፣ ባትሪዎች፣ ፍላፖች፣ ከነመዳሪዎች፣ጀኔረተሮች፣በርሜሎች፣ በርሜሎች ከነክዳናቸው የህከምና እቃዎች የአንዱን መስሪያ ቤት በአይነት የተቀመጡትን በጥቅል መጫረት አለባቸው፡
  7. ተጫራቾች ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ድረስ በመሄድ ንብረቱን አይተው መጫረት ወይም ዋጋ መስጠት አለባቸው፡፡ነገር ግን ንብረቱን ሳያዩ ቢጫረቱና ቅሬታ ቢቀርብ አገልግሎቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡
  8.  ለሚገዙት የተለያዩ ተቋማት ተሸከርካሪዎችና በቁርጥራጭ መልክ የሚወገዱ ተሸከርካሪዎች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20 በመቶ (20%)፣ ሌሎችን ንብረቶችን፣ ደግሞ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ሲ.ፒ.ኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  9.  የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 504 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም፡፡
  11. ተሽከርካሪዎች የነበረባቸው የቦሎ ዕዳ እና የስም ዝውውር ወጪ በአሸናፊ ተጫራቾች ይሸፈናል፡፡
  12. አንድ ተጫራች አንድ ተሽከርካሪ እና ከአንድ የመ/ቤት ንብረቶች በላይ መግዛት ይችላል፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራች ለአንድ ተሽከርካሪ፤ ለአንድ መደብ ንብረት የተለያየ ዋጋ በመስጠት መወዳደር አይችልም፡፡
  13. በመነሻ ዋጋና በታች የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
  14. የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ ኮድ ወይም መለያ ቁጥር ሲጽፍ ተሳስቻለሁ ወይም ሳልጽፍ ቀርቻለሁ የሚሉ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
  15. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለአገልግሎቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
  16. ንብረቱን በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
  17. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ከጨረታው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋ ማሻሻል ወይም መለወጥ አይችልም፡፡
  18.  የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውም ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

 ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-557-86-71 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አገልግሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-26 10:15
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡15 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Government Procurement and Property Disposal Service
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Aug 08, 2026)
  • Posted at: 2026-08-08T08:27:54.000Z
← Back to all tenders