Stationery
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር 001/2019
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ
- የሰራተኞች ከበብ
- አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች እስቴሽነሪ/
- የፅዳት እቃዎች
- የደንብ ልብስ
- የኮምፒውተር መለዋወጫ ከነጥገናው
- የደንብ ልብስ ስፌት
- የግብርና እቃዎች
- ትራንስፖርት /ሀይገር ታታ ሚኒባስ ሀይሩፍ/ ደርሶ መልስና ሙሉ ቀን ማቅረብ የሚችል
- ዲኮር እና ድንኳን ኪራይ
- የህትመት ስራ
- ቋሚ እቃዎች /ኤሌክትሮኒክስ
- የጭነት መኪና /አይሱዙ/
- የእፅዋት ዘር እና መድሃኒት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች መወዳደር ትችላላችሁ።
- በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
2. ተጫራቾች በተጨማሪ ታክስ(VAT) ከፋይ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ
3. በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
4. ለሎት 1 ብቻ ቫት ወይም ቲኦቲ ከፋይ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ
5.ለሎት 12 ብቻ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ቲን ነበር እና ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ።
6. ተጫራቾች ለሚጫረቱት እቃዎች በሙሉ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል እንዲሁም አንድ ናሙና ላይ ሁለት እቃ ማቅረብ ከውድድር ውጪ ያደርጋል። ናሙና መቅረብ ለማይቻል እቃዎች ብቻ በፎቶ የተደገፈ መረጃ ማቅረብ አለበት። ናሙናዎችንም እስከ 6 ወር ድረስ መልሰው ካልወሰዱ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
7. አንዱ በአንዱ ዋጋ ላይ ተነስቶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከታች በሰንጠረዡ እንደተዘረዘረው በእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ መሰረት በስሙ የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡(CPO) ከኦርጅናል ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።
|
ሎት ቁጥር
|
የሎት ዝርዝር
|
የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በኢትዮጵያ ብር |
ምርመራ
|
|
ሎት 1 |
የሰራተኞች ክበብ
|
5,000.00
|
ከአንድ ሎት በላይ የሚወዳደር ተወዳዳሪ ሲፒኦ ለእያንዳንዱ በተናጠል ነው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው
|
|
ሎት2 |
አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች/ እስቴሽነሪ/ |
25,000.00
|
|
|
ሎት3 |
የፅዳት እቃዎች
|
20,000.00
|
|
|
ሎት4 |
የደንብ ልብስ
|
15,000.00
|
|
|
ሎት5 |
የኮምፒውተር መለዋወጫ ከነጥገናው |
5,000.00
|
|
|
ሎት6 |
የደንብ ልብስ ስፌት
|
3,000.00
|
|
|
ሎት7 |
የግብርና እቃዎች
|
5,000.00
|
|
|
ሎት8 |
ትራንስፖርት
|
5,000.00
|
|
|
ሎት9 |
ዲኮርና ድንኳን ኪራይ
|
5,000.00
|
|
|
ሎት10 |
የህትመት ስራ
|
5,000.00
|
|
|
ሎት11 |
ቋሚ እቃዎች /ኤሌክትሮኒክስ/
|
15,000.00
|
|
|
ሎት12 |
የጭነት መኪና /አይሱዙ/
|
3,000.00
|
|
|
ሎት13 |
የእፅዋት ዘር እና መድሃኒት |
5,000.00
|
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የሚቆይ ይሆናል። ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነትቶች በሎት የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ 500 /አምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር/ በመክፈል በጉ/ክ/ከተማ ወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት ግ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት የቢሮ ቁጥር 305 በመቅረብ መውሰድ ይቻላል።
10. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው እራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚቀርብበት ዕቃ ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጀ ምርት/ዕቃ ከገበያ ላይ ገዝተው የሚወዳደሩ እንደ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
11. በስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ ማስረጃ በማቅረብ የሚወዳደሩ ድርጅቶች የጨረታ ሰነድ ብቻ በነፃ የሚሰጥ ሲሆን ከላይ ለተዘረዘሩት የጨረታ ሎቶች ሲፒኦ ያላቀረቡ ተጫራቾች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ።
12. ተጫራቾች ሁሉንም የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒውን ለየብቻ ታሽጎ በሚመለከተው ኃላፊ ተፈርሞና የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጠቀስ አለበት ያልተጠቀሰ ከሆነ ቫት እንዳካተተ ይወሰዳል።
13. ጽ/ቤቱ የሚገዛቸውን እቃዎች ከውል በፊት የእቃውን ብዛት 20% ከውል በኋላ 25% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል።
14. ተጫራቾች ባሸነፉት አጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
15. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፏቸውን እቃዎች በውላቸው መሰረት ሙሉ ለሙሉ በራሳቸው ትራንስፖርት ጽ/ቤቱ ድረስ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
16. አገልግሎት ላይ ያሉት ለአንድ ዓመት ውል ለመግባት ፍቃደኛ የሆኑ መሆን አለበት።
17. ስርዝ ድልዝ መረጃዎች እና አንድ እቃ ላይ ሁለት ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የላቸውም።
18. ጨረታው በ10ኛው ቀን 10:30 ሰአት ታሽጎ በማግስቱ 4 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጉ/ክ/ከ/ወ/ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 305 የሚከፈት ሲሆን ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
19. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ከ7 የቅሬታ ቀናት በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% በማምጣት ከ8-15 ባሉት ቀናት ውስጥ ውል መዋዋል አለባቸው።
20. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
21. በጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለጹ ካሉ በግዥ መመሪያ መሠረት ተፈፃሚ ይሆናሉ።
- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት አስኮ ከጨረታ አለፍ ብሎ ፖሊስ ጣቢያው ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ ቢሮ ቁጥር 305 ላይ ይገኛል
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 827 8749 / 011 827- 8662
ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-20
- Bid closing time: 16:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 10:30 ሰአት
- Bid opening: 2026-08-21 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 10:30 ሰአት ታሽጎ በማግስቱ 4 ሰአት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Gulele Sub City Administration Woreda 5 FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: ለእያንዳንዱ 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T07:18:27.000Z