Catering and Cafeteria Services

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 የሚገኘው ዕድገት አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቋሚና አላቂ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በውስን ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር ፡- ዕድመግጨ/001/2019

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 የሚገኘው ዕድገት አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጉትን ቋሚና አላቂ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በውስን ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችው እና ማቅረብ የሚችሉ

2. ኪውአር ኮድ ደረሰኝ ተጠቃሚ የሆነ

3. የዘመኑን የግብር የከፈለ

4. በራሱ ወጪ ለምግብ ቤት አገልግሎት የሚያስፈልጉ ዕቃዎችንና አገልግሎቶቹን አቅርቦ መስራት የሚችል።

5. ለት/ቤቱ ማህበረሰብ አገልግሎት የሚውሉ የተሟላ የክበብ አገልግሎቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ፣በጥራት እና በሚፈለገው ዓይነት ማቅረብ የሚችል

6. አስፈላጊ የሆኑ ከንግድ ስራው ጋር ተያያዥ የሆኑ የመንግስት ግብርና ቀረጥ ወጪዎችን በራሱ መክፈል የሚችል።

7. መንግስት ባስቀመጠው ገቢዎች አነስተኛ ነጋዴዎችን በሚመለከት ባወጣው መመሪያ መሰረት እንቀበላለን።

8. የውሃና መብራት ፍጆታ ክፍያ በተከራይ የሚሸፈን ይሆናል።

9. በተለያየ ጥፋቶች ያልታገደ።

ማንኛውም ተጫራች ይህ የጨረታ ሰነድ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር የስራ ቀናት ውስጥ በዕድገት አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በመገኘት 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

ማንኛውንም ተጫራች ከዚህ በታች በተጠቀሰው ሎት መሰረት በዕድገት አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ስም የተሰራ የጨረታ ማስረከቢያ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

ሎት

 

የዕቃው የአገልግሎቱ መግለጫ

የመደብ ኮድ

 

የተሰራበት ፐርሰንት

ሲፒኦ ( ብር)

 

1

የሰራተኞች መስተግዶ አገልግሎት

6233

1%

11,000

ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሰነድን ክፍል 4 ( የጨረታ ሰነድ ቅፆች ) ክፍል 6 (ፍላጎት መግለጫ ) ሙሉ በሙሉ በመሙላት እና ሙሉ የጨረታ ሰነድ አንድ ኮፒ በማደረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት አስር የስራ ቀናት በዕድገት አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባችሁ ፡፡

ጨረታው ይህ የጨረታ ሰነድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 መድኃኒዓለም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አደባባይ የግሩም ሆስፒታል ታክሲ መያዣ ፊት ለፊት ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 2 73 47 58 ወይም 011 2 13 50 35 ዘወትር በስራ ሰዓት በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ት/ጽ/ቤት ዕድገት አንደኛና
መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-21
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ የጨረታ ሰነድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30
  • Bid opening: 2026-08-21 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ የጨረታ ሰነድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን 4፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Edget Primary and Secondary School
  • Bid bond: የተሰራበት ፐርሰንት 1% ሲፒኦ፤ (ብር) 11,000
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
  • Posted at: 2026-08-10T07:28:04.000Z
← Back to all tenders