Property and building foreclosure

ስፋቱ 73 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

በድጋሚ የወጣ

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እነ አቶ ሚካኤል ዘውዴ እና በፍ/ባለዕዳ ኤስሮም አንዳርጌ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.209487 በቀን 18/11/2016ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.254558 በቀን 21/02/2017ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በአራዳ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 557 የሆነ የይዞታው ስፋት ሌሎች ፍርድ ያላረፈባቸውን ቤቶች ጨምሮ በፕሮፖርሽን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው ስፋት 73 ካ/ሜ ቤቱ ያረፈበት 146 ካሜ በጠቅላላ በፕሮፖርሽን ለግለሰቡ የሚደርሰው ስፋት 219 ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ 10,254,894 (አስር ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ አራት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና አራት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/ መ/ቁ.254558 በቀን 15//2018ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1/4ኛ 2,563,723.50 ( ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ ሶስት ከ50/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ግዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4  ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ5 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ  መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-18
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-09-18 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
  • Posted at: 2026-08-10T07:36:55.000Z
← Back to all tenders