Stationery and office consumables
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወ/01 የአብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2019 በጀት አመት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወ/01 የአብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2019 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግዥው ዓይነት
- ሎት 1 -የፅህፈት አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የት/ት አላቂ ዕቃዎች እና ለመዋለ ህፃናት የሚያገለግሉ የት/ት ዕቃዎች፣ የስፖርት ትጥቅ እና ለስፖርት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች፣ ህትመት እንዲሁም አጋዥ መፅሐፎች እና የጥገና ዕቃዎች፣ የመጀመሪያ የህክምና መርጃ እና የቤተ-ሙከራ የሚያስፈልጉ Chemicals እና ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት2፡ የፅዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 3፡- የደንብ ልብስና ማሰፊያ
- ሎት 4፡- ሜንቴናንስ የኮምፒዩተር እና የፕሪንተር፣ ማባዣና ፎቶ ኮፒ ማሽኖች ጥገና ፣የኤሌትሪክ መስመር የተለያዩ ብልሽት ጥገና፣ የውሃ መስመር ብልሽት ጥገና በአጠቃላይ ሁለገብ የሆነ የአገልግሎት ሠራተኛ
- ሎት 5፡ ለስልጠና መስተንግዶ
ከላይ በተጠቀሰው መሠረት መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።
1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የአገር ውስጥ ገቢ እና የዘመኑ ግብር አጠናቀው የከፈሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይና በአቅራቢዎች ላይ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
3. የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ከላይ ከሎት 1-3 በተዘረዘረው መሰረት ሁሉም ሎት እያንዳንዳቸው ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር /ሲሆን 4 እና 5 ደግሞ በ200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት በቂ/ክ/ከ/ወ/01 የአብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁ. 002/5 መግዛት ይችላሉ።
4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በሎት በተዘረዘረው መሰረት ከሎት1-3 እያንዳንዳቸው ብር 3000.00 /ሶስት ሺ ብር / ሲሆን ሎት 4 እና 5 ደግሞ ብር 1500.00 /አንድ ሺ አምስት መቶ ብር/ ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው የአብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁ. 002/5 ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
7. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ከናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በቀረበው ናሙና መሠረት የማምጣት ግዴታ አለባቸው።
8. ክፍያው የሚፈፀመው ለሚያቀርቡት ዕቃ ሙሉ በሙሉ ለት/ቤቱ ሲያስረክቡና የቀረበው ዕቃ ጥራቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
9. ጨረታው በተዘጋ ማግስት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በቂ/ክ/ከ/አብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ የመ/ደ/ት/ቤት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 002/5 የሚከፈት ይሆናል።
10. ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድቅ ይሆናል።
11. ከላይ ከሎት 1-3 የተዘረዘሩት ዕቃዎች ናሙና ያስፈልጋቸዋል ለኤሌክትሮኒክስ ደግሞ በስዕል የተደገፈ መሆን አለበት።
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- ኦሎምፒያ ዳይሉክስ ፈርኒቸር ቀደም ሲል በነበረው አሁን በሆነው አድማስ ኮሌጅ ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡-011 551 0765/ 011 557 9925 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወ/01 የአብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-20
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት
- Bid opening: 2026-08-21 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ ጨረታው በተዘጋ ማግስት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kirkos Sub City Education Bureau Abiyot Eremja Elementary School
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T07:55:23.000Z